ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ቀሪ የአንድ ዓመት ውል እያለው በስምምነት የተለያየው ግብ ጠባቂ ኢትዮጵያ መድንን ተቀላቅሏል

በአሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ የሚሰለጥኑ ኢትዮጵያ መድኖች ወደ ዝውውሩ በመግባት አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም እና የነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል በማራዘም ቡድናቸውን በማጠናከር እንደሚገኙ ይታወቃል ፤ አሁን ደግሞ ግብ ጠባቂው አሸብር ተስፋዬን ማስፈረማቸው አውቀናል።
በ2016 በነገሌ አርሲ ቆይታቅ የከፍተኛ ሊጉ የዓመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ ክብርን ያገኘው የግብ ዘቡ የተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ካሳለፈ በኋላ አሁን በሁለት ዓመት ውል ወደ መድን መፈረሙን አውቀናል ።

