ሁለገቡ ተጫዋች ለኢትዮጵያ መድን ፈርሟል

ሁለገቡ ተጫዋች ለኢትዮጵያ መድን ፈርሟል

በወላይታ ድቻ ጋር ቆይታ የነበረው ሁለገቡ ተጫዋች ኢትዮጵያ መድንን ተቀላቅሏል

ቀደም ብለው የግብ ጠባቂውን አሸብር ተስፋዬ እና የአጥቂውን ሙሐባ አደምን ዝውውር ያጠናቀቁት ኢትዮጵያ መድኖች አሁን ደግሞ ሁለገቡን የመስመር ተጫዋች አማኑኤል አሊሶን ማስፈረማቸው እርግጥ ሆኗል።

ነገሌ አርሲ ወደ ፕሪምየር ሊግ ሲያድግ የስብስቡ አካል የነበረው ተጫዋቹ በግራ መስመር ተከላካይነት እንዲሁም በአጥቂነት መጫወት የሚችል ሲሆን ከዚህ ቀደም ደግሞ በቦዲቲ ከተማ ፣ በአዲስ አበባ ከተማ እና በተጠናቀቀው ዓመት በወላይታ ድቻ መጫወት ችሏል። አሁን ደግሞ በወላይታ ድቻ ምክትል አሰልጣኝ በመሆን አብረውት ከሰሩት አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ ጋር ዳግም ለመስራት ወደ ኢትዮጵያ መድንን ተቀላቅሏል።