በርበሬዎቹ የቀድሞ አሰልጣኛቸውን ለመሾም ተቃርበዋል

በርበሬዎቹ የቀድሞ አሰልጣኛቸውን ለመሾም ተቃርበዋል

አዲስ አዳጊዎቹ ሀላባ ከተማዎች አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም ከጫፍ መድረሳቸውን አውቀናል

ከዓመታት ጥበቃ በኋላ ወደ ሊጉ ያደጉት ሀላባዎች ከአሰልጣኝ በሽር ጋር ሊቀጥሉ እንደማይችሉ እና የአሰልጣኝ በሽር ውሳኔ እንደሚጠበቅ አስቀድመን ባጋራናቹሁ መረጃ መግለፃችን የሚታወቅ ሲሆን ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባገኘችው መረጃ አሰልጣኝ ካሊድ መሐመድ አዲሱ የበርበሬዎቹ አለቃ ሆነው ለመሾም መቃረባቸውን አውቀናል። በአሰልጣኝ ካሊድ እና በበርበሬዎቹ መካከል ያለው ድርድር እስካሁን ድረስ በጥሩ መንገድ እየሄደ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ደግሞ ሹመታቸው ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል።

አሰልጣኝ ካሊድ መሐመድ በተጫዋችነት ዘመኑ በተለያዩ ክለቦች እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጫወት ጥሩ ጊዜ ያሳለፈ ሲሆን ወደ አሰልጣኝነት ሞያ ከገባ በኋላም በኢትዮጵያ ቡና በምክትል እና በዋና እንዲሁም በዳሽን በማስከተል ደግሞ ወደ ከፍተኛ ሊግ በማምራት ያለፉትን ዓመታት ቡታጅራ ከተማ፣ ሀላባ ከተማ፣ ወልድያ ከተማ በማሰልጠን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ሀድያ ሆሳዕናን ማሰልጠናቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ዳግም ወደ ቀድሞ ክለባቸው ለመመለስ መቃረባቸው ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።