የሲዳማ ቡና ሦስት ወሳኝ ተጫዋቾች ከቡድኑ ጋር አይገኙም

የሲዳማ ቡና ሦስት ወሳኝ ተጫዋቾች ከቡድኑ ጋር አይገኙም

የፊታችን እሁድ የቻምፒየንስ ሊጉ ወሳኝ ጨዋታ የሚጠብቃቸው ሲዳማ ቡናዎች ሦስት ተጫዋቾቻቸው ከቡድኑ ጋር እንደማይገኙ አረጋግጠናል።

በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር የማጣርያ ጨዋታቸውን ከሱዳኑ ክለብ አል ሂላል ጋር የፊታችን እሁድ ጥቅምት 8 ቀን በድሬደዋ ስታዲየም የሚያደርጉት ሲዳማ ቡናዎች ዛሬ ድሬደዋ ከተማ ገብተዋል።

አመሻሽ ላይ በድሬደዋ ስታዲየም የመጀመርያ ልምምዳቸውን የሰሩት ሲዳማ ቡናዎች ሦስት ወሳኝ ተጫዋቾቻቸው በልምምዱ ወቅት እንዳልተገኙ ሶከር ኢትዮጵያ በቦታው በመገኘት አረጋግጣለች። በልምምዱ ላይ ያልተገኙት ተጫዋቾች አንበሉ ያሬድ ባዬ፣ መስፍን ታፈሰ እና ቢንያም በላይ ናቸው።

አንበሉ ያሬድ ባዬ እና መስፍን ታፈሰ በከቡድኑ ጋር ድሬደዋ አብረው ቢመጡም በንግድ በባንኩ ጨዋታ ወቅት ባጋጠማቸው ጉዳት ምክንያት የህክምመና ምርመራ ያደረጉ ሲሆን ውጤቱ ነገ እንደሚታወቅ ሰምተናል። ይን ተከትሎ ከውጤቱ በኋላ ከቡድኑ ጋር ይቀላቀላሉ ወይስ አይቀላቀሉም የሚለውን ከውሳኔ እንደሚደረስ አውቀናል። የአማካይ ቢንያም በላይ በዛሬው ልምምድ ብቻ ሳይሆን ከንግድ ባንክ ጋር በነበረው ጨዋታ ላይም ከቡድኑ አስተላለፍ ውጪ የነበረ ሲሆን ምክንያቱ ከጉዳት ጋር ያልተያያዘ እንደሆነ እና በግል ጉዳይ እንደሆነ አውቀናል።

ሶከር ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ የሚኖሩ አዳዲስ መረጃዎችን በቀጣይ ልምመዶች ላይ በመገኘት ተከታትላ ወደ እናተ የምታደርስ ይሆናል።