በኢትዮጵያ ፐሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት ዛሬ በተካሄዱ 5 ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ አሸንፎ ከመሪው ጋር ያለውን ርቀት ሲያጠብ ዳሽን እና ሙገር ሲሚንቶም በሜዳዳው ድል ቀንቷቸዋል፡፡
8 ሰአት አበበ ቢቂላ ላይ ወላይታ ድቻን ያስተናገደው ኤሌክትሪክ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡ ወላይታ ድቻ አዲሱ ተስፋዬ በግንባሩ ገጭቶ ባስቆጠረው ግብ 1-0 ቢመራም ኤሌክትሪክ ዊልያም ኤሳድጆ ባስቆጠረው ግሩም የቮሊ ግብ አቻ ለመሆን በቅቷል፡፡
በ9 አሰት ጎንደር ላይ በተደረገው የዳሽን ቢራ እና ሀዋሳ ከነማ ጨዋታ ዳሽን በራ 2-1 አሸንፏል፡፡ ሀዋሳ ከነማ ተመስገን ተክሌ በ44ናው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ 1-0 ሲመራ ቢቆይም ሚካኤል ጆርጅ በ45ኛው እና አሌክስ በ90ኛው ደቂቃ ባስቆጠሩት ግብ ዳሽን በራ ጨዋታውን 2-1 አሸንፎ ወጥቷል፡፡
በተመሳሳይ ሰአት አሰላ ላይ መከላከያን ያስተናገደው ሙገር ሲሚንቶ በሄኖክ ፍስሃ ግብ 1-0 ሲያሸንፍ አርባምንጭ ላይ አርባምንጭ ከነማ ከ አዳማ ከነማ ካለግብ 0-0 ተለያይተዋል፡፡
አበበ ቢቂላ ላይ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶት በነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ደደቢት ጨዋታ ፈረሰኞቹ በቀላሉ 2-0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል፡፡ የቅዱስ ጊዮዮጊስን ቀዳሚ ግብ ተከላካዩ ሳላዲን ባርጊቾ በግሩም ሁኔኔ ሲያስቆጥር አሉላ ግርማ በሁለተኛው አጋማሽ ተጨማሪዋን ግብ አስቆጥሯል፡፡
ትላንት በተደረጉ ጨዋታዎች ኢትዮጵያa ቡና ወልድያን 5-2 ሲያሸንፍ ንግድ ባንክ ከ ሲዳማ ቡና 1-1 አቻ ተለያይተዋል፡፡
ሊጉ በመጪው እሁድe በተስተካካይ ጨዋታዎች ሲቀጥል ቦዲቲ ላይ ወላይታ ድቻ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከነማ ከ ደደቢት ፤ አበበ ቢቂላ ላይ ኢትዮጵያ ቡና ከ ኤሌክትሪክ ተጫውተው 1ኛው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ይዘጋል፡፡
ሊጉን ሲዳማ ቡና በ27 ነጥቦች ሲመራ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ24 ይከተላል፡፡ የከፍተኛ ግብ አግቢነቱን ቢንያም አሰፋ በ11 ግብ ይመራል፡፡