FT
|
አአ ከተማ | 0-2
|
ፋሲል ከተማ |
– 6′ 32′ ኤዶም ኮድዞ (ፍ.ቅ.ም)
ተጠናቀቀ!!!!
ጨዋታው በእንግዳዎቹ ፋሲል ከተማዎች 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ቢጫ ካርድ
90+3′ ዘሪሁን ብርሃኑ የቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡
90′ ተጨማሪ 4 ደቂቃ
87′ ሙሀጅር መኪ በግምት ከ25 ሜትር ርቀት የተገኘውን ቅጣት ምት በቀጥታ ሞክሮ ኳሷን ዮሀንስ ሽኩር በግሩም ሆኒታ አድኖበታል፡፡
87′ የተጫዋች ለውጥ- ፋሲል ከተማ
ኤዶም ሆሶሮቪ ወጥቶ ሙሉቀን ታሪኩ ገብቷል፡፡
80′ በተለምዶ ካታንጋ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በብዛት ሰብሰብ ብለው የሚገኙት የፋሲል ከተማ ደጋፊዎች ቡድናቸውን ባስገራሚ ሆኒታ እያበረታቱ ይገኛል፡፡
78′ የተጨዋች ለውጥ- ፋሲል ከተማ
ሰለሞን ገብረመድህን ወጥቶ ኤፍሬም አለሙ ገብቷል።
69′ ሀይሌ እሸቱ በግሩም ሆኒታ ተመስርቶ የመጣውን ኳስ ቢያስቆጥርም ከጨዋታ ውጪ አቋቋም ላይ በመገኘቱ ሳይፀድቅ ቀርቷል።
63’የተጨዋች ለውጥ -አዲስ አበባ ከተማ
አቤል ዘውዱ ወጥቶ ሙሀጅር መኪ ገብቷል።
58′ ሰለሞን ገብረመድህን ከሳጥኑ ውጪ ወደግብ የመታው ኳስ የግቡን አግዳሚ ለትሞ ወጥቷል።
52′ እንየው ከቀኝ መስመር ያሻማውን የማእዘን ምት ዲሜጥሮስ ገጭቶ ለጥቂት ከግቡ አናት በላይ ወጥቷል።
48′ ናትናኤል ጋንቹላ ከኤዶም ተቀብሎ የመታውን ኳስ ተክለማርያም በቀላሉ ይዞታል።
46′ ሁለተኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀምሯል።
የተጫዋች ለውጥ – አዲስ አበባ ከተማ
አማረ በቀለ ወጥቶ ዘሪሁን ብርሃኑ ገብቷል።
የተጫዋች ለውጥ – ፋሲል ከተማ
ኤርሚያስ ሀይሉ ወጥቶ አብዱራህማን ሙባረክ ገብቷል።
የመጀመሪያው አጋማሽ በፋሲል ከተማ 2-0 መሪነት ተጠናቋል።
45′ ተጨማሪ ሰዐት – 2 ደቂቃ
43′ ሰለሞን ገብረመድህን ከሳጥኑ ጠርዝ ላይ በቮሊ ወደግብ የመታው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል።
40′ ፍቅረሚካኤል ዓለሙ ያሻማውን ቅጣት ምት ተክለማርያም ሻንቆ ይዞታል።
32′ ጎል!!!!
ሔኖክ ገምቴሳ መሬት ለመሬት ያሻገረውን ኳስ ኤዶም ኮድዞ በቀላሉ ወደግብ ቀይሮታል።
28′ ኤፍሬም ቀሬ በቀኝ መስመር በኩል ወደግብ የመታው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል።
23′ ሰዒድ ሃሰን ያሻማው ኳስ በግብ ጠባቂው ፊት ነጥሮ ወደግብ ቢሄድም ተተክለማርያም ሻንቆ እንደምንም በጣቶቹ ጫፍ ነክቶ አውጥቶታል።
21′ ኤፍሬም ቀሬ ከሳጥኑ ውጪ አክርሮ የመታው ኳስ ዒላማውን ሳይጠብቅ ቀርቷል።
18′ ምንያምር ጴጥሮስ በቀኝ ክንፍ በኩል ከርቀት በቮሊ የመታው ኳስ የግቡን አግዳሚ ለትሞ ወጥቷል።
14′ ኤርሚያስ ሀይሉ ከሳጥኑ ውጪ የመታው ኳስ ከግቡ አናት በላይ ወጥቷል።
11′ ሔኖክ ገምቴሳ ከቀኝ መስመር ያሻገረውን ጥሩ ኳስ ኤዶም ሳይደርስበት ቀርቷል።
6′ ጎል!!!!
ኤዶም ኮድዞ ፍፁም ቅጣት ምቱን በአግባቡ በመጠቀም ፋሲል ከተማን መሪ አድርጓል።
5′ ዲሚጥሮስ ወልደስላሴ በሳጥኑ ውስጥ ኳስን በእጁ በመንካቱ ፍፁም ቅጣት ምት ለፋሲል ከተማ ተሰጥቷል።
1′ ጨዋታው በፋሲል ከተማ አማካኝነት ተጀምሯል።
የመጀመሪያ አሰላለፍ – አዲስ አበባ ከተማ
1 ተክለማርያም ሻንቆ
7 ምንያምር ጲጥሮስ – 20 ሰይፈ መገርሳ – 70 ዲሚጥሮስ ወልደስላሴ – 77 አማረ በቀለ
40 ዳዊት ማሞ – 2 እንየው ካሳሁን – 90 አቤል ዘውዱ – 10 ዮናታን ብርሃነ
53 ኤፍሬም ቀሬ – 8′ ኃይሌ እሸቱ
ተጠባባቂዎች
98 ደረጀ ዓለሙ
81 አለማየሁ ሙለታ
6 ጊት ጋትኮች
80 ከነዓን መርክነህ
30 ሙሃጅር መኪ
83 ፀጋ አለማየሁ
13 ዘሪሁን ብርሃኑ
የመጀመሪያ አሰላለፍ – ፋሲል ከተማ
93 ዮሃንስ ሽኩር
28 ሰኢድ ሁሴን – 5 ታደለ ባይሳ – 21 ከድር ኸይረዲን – 4 ፍቅረሚካኤል አለሙ
98 ሰለሞን ገብረመድህን – 26 ሄኖክ ገምተሳ – 7 ፍፁም ከበደ
99 ኤርምያስ ሃይሉ – 94 ኤዶም ሆሮሶውቪ – 20 ናትናኤል ጋንጂላ
ተጠባባቂዎች
1 ምንተስኖት አድጎ
6 ኤፍሬም አለሙ
17 ይስሃቅ መኩሪያ
10 ሙሉቀን ታሪኩ
24 ያሬድ ዝናቡ
18 አብዱራህማን ሙባረክ
56 ገዛኸኝ እንዳለ