የፕሪምየር ሊጉ ተስተካካይ ጨዋታዎች የሚደረጉበት ቀን ይፋ ሆኗል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች የሚደረጉበትን ቀናት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሊግ ኮሚቴ ይፋ አድርጓል፡፡

በ2ኛው ሳምንት ሊጫወቱ ፕሮግራም ወጥቶላቸው የነበረው የፋሲል ከተማ ከ ወላይታ ድቻ እንዲሁምየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታዎች በመጪው ወር መጀመርያ የካቲት 2 ቀን 2009 እንዲጀመሩ ተወስኗል፡፡

የፕሪምየር ሊጉ የመጀመርያ ዙር እሁድ ጥር 28 ቀን 2009 እንደሚጠናቀቅ የሊጉ መርሃግብር ያሳያል፡፡ ይህን ተከትሎም ሁለቱ ጨዋታዎች ከዙሩ መጠናቀቅ በኋላ ይካሄዳሉ ማለት ነው፡፡

ሶከር ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ሁለቱ ጨዋታዎች የሊጉ አንደኛ ዙር ከተጠናቀቀ በኋላ እንደሚካሄድ መዘገቧ የሚታወስ ነው፡፡

ሀሙስ የካቲት 2 ቀን 2009

ፋሲል ከተማ ከ ወላይታ ድቻ (አጼ ፋሲለደስ ስታድየም)

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ሀዋሳ ከተማ (አአ ስታድየም)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *