የይርጋለሙ ክለብ ሲዳማ ቡና የፊት አጥቂው በረከት አዲሱ ላይ የሁለት አመት እገዳ መጣሉ ታውቋል፡፡
ሶከር ኢትዮጵያ ባረጋገጠችው መረጃ መሰረት በረከት አዲሱ ለሌሎች የክለቡ ተጨዋቾች አርአያ የማይሆን የክለቡን ስምና ክብር የሚያጎድፍ ተግባር ሲፈፅም ደርሼበታለው በማለት ለሁለት አመት ምንም አይነት ግልጋሎት እንዳይሰጥ የዲሲፒሊን ቅጣት አስተላልፎበታል፡፡
ከእግር ኳስ ህይወቱ በስተጀርባ ከባድ ጉዳቶች እና ውዝግቦች የማያጡት የቀድሞው የንግድ ባንክ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና አዳማ ከተማ አጥቂ ባለፈው የውድድር ዘመንም ከአሰልጣኙ ጋር በተፈጠረ ልዩነት ለክለቡ እምብዛም ግልጋሎት መስጠት አልቻለም ነበር፡፡