CHAN 2016: በቻን ማጣርያ ኢትዮጵያ ከ ኬንያ ትጫወታለች

በሃገር ውስጥ ሊጎች በተውጣጡ ተጫዋቾች ብቻ የሚካሄደው የ2016 የአፍሪካ ሃገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) የማጣርያ ድልድል ዛሬ ወጥቷል፡፡ በድልድሉ ፕሮግራም ላይ የካፍ ዋና ፀሃፊ ሃኪም ኤል አምራኒ እና የቻን አዘጋጅ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት የሆኑት አልማሚ ካማራ ተገኝተዋል፡፡

በ2014ቱ ውድድር የተሳተፈችው ኢትዮጵያ በምስራቅ እና መካከለኛው ዞን ቅድመ ማጣርያ ከኬንያ ጋር የተደለደለች ሲሆን የመጀመርያ ጨዋታዋንም ኤፕሪል 20 ወይም 21/2015 ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ኢትዮጵያ ኬንያን አሸንፋ ወደ ቀጣዩ ዙር የምታልፍ ከሆነ የቡሩንዲ እና ጅቡቲ አሸናፊን ትገጥማለች፡፡

የቻን ውድድር በጃንወሪ 2016 በምስራቅ አፍሪካዊቷ ሃገር ሩዋንዳ አስተናጋጅነት ይካሄዳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *