CHAN 2016: ‹‹ በድልድሉ ደስተኞች ነን ›› ጁነይዲ ባሻ

ዛሬ በወጣው የአፍሪካ ሃገራት ቻምፒዮንሺፕ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በቅድመ ማጣርያው ከኬንያ አቻው ጋር መደልደሉን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ጁነይዲ ባሻ ለካፍ ኦንላይን ስለ ድልድሉ የተሰማቸውን ተናግረዋል፡፡

‹‹ ድልድሉ ጥሩ የሚባል ነው፡፡ ከጎረቤታችን ኬንያ ብሄራዊ ቡድን ጋር በመደልደላችንም ደስተኞች ነን፡፡ በእግርኳሱ ተመሳሳይ የሚባል ደረጃ ላይ እንገኛለን፡፡ ውድድሩ ጠንካራ እና ለተጫዋቾቻንም ጥሩ እድል የመኒፈጥር ውድድር ነው፡፡ ባለፈው የኢኳቶርያል ጊኒ የአፍሪካ ዋንጫ ባለመሳተፋችን የማናስበው ይህንን ማጣርያ ስለማለፍ ነው፡፡ ›› ሲሉ ፕሬዝዳንቱ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *