የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3-0 ኤሌክትሪክ ፡ ታክቲካዊ ትንታኔ

በሚልኪያስ አበራ

 

እንግሊዛዊው ታዋቂ የእግርኳስ ታክቲክ ፀሃፊ ጆናታን ዊልሰን ‹‹ formations are neutrals ›› የሚላት ታዋቂ አባባል አለችው፡፡ የተጫዋቾች የሜዳ ላይ የታክቲክ አተገባበር እንጂ ቁጥራዊ የቅርፅ ወይም የመዋቅር አደራደራቸው በውጤት ላይ ያለው ፋይዳ አናሳ መሆኑን ሲያስረዳ፡፡ ሃሳቡ እኔንም ይስማማኛል፡፡ ሆኖም እንደ መነሻ ተጋጣሚ ቡድኖች የሚጫወቱበትን ፎርሜሽን ማወቅና መለየት መቻል አስፈላጊ ነው ባይ ነኝ፡፡

እንደተለመደው በዚህኛውም ጨዋታ የሁለቱን የአዲስ አበባ ክለቦች ፍልሚያ ትንታኔ መግቢያ በተጫዋቾች የሜዳ ላይ አደራደር እጀምራለሁ፡፡

ሁለተኛው ዙር ከተጀመረ አንስቶ ስኬታማ ጉዞ እያደረገ የሚገኘው ንግድ ባንክ 4-2-3-1 ን በሙሉ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሲጠቀም በውድድር ዘመኑ ወጥ አቋም ማሳየት የተሳነው ኤሌክትሪክ ደግሞ 4-4-2 (ወደ 4-1-3-2 ሲቀየር ይስተዋላል) ተግብሯል፡፡

(ምስል 1)

 

የንግድ ባንክ double pivots

በዘመናዊው እግርኳስ double pivotes የበለጠ ሚዛናዊ የሆነ የ4-2-3-1 ፎርሜሽን አጠቃቀምን ያስገኛሉ፡፡ በዚህ የተጫዋቾች የሜዳ ላይ አደራደር ስርአት ሁለቱ የተከላካይ አማካዮች በንፅፅር በሚቀያየር የጨዋታ ሒደቶች (የማጥቃት እና የመከላከል አጨዋወቶች) የሚኖራቸው የመተካካት ሚና ለቡድኑ ውጤታመ፣ነት አይነተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡

ከሁለቱ አማካዮች አንደኛው በመከላከል ላይ ሲያተኩር ሌላኛው ደግሞ በማጥቃት አጨዋወት ላይ ተሳታፊ የሚሆንበትን መንገድ ያመቻቻል፡፡ከፊቱ ያሉት የማጥቃት አማካዮች ፣ overlap የሚያደርጉ የመስመር ተከላካዮች እና አጥቂው የሚፈጥሩትን ክፍተት (space) ለመድፈን ይጥራል፡፡ ይህም የቡድኑን የግብ እድሎች የመፍጠር ፣ የመጠቀም እንዲሁም የማስቆጠር አቅምን ይጨምራል፡፡

የማጥቀትም ሆነ የመከላከልን ሐላፊነት ሁለቱም የተከላካይ አማካዮች በተቀያያሪነት እና በከፍተኛ መግባባት ይከውናሉ፡፡ የአጥቂ መስመር የተጋጣሚን ተከላካዮች ወደራሳቸው የግብ ክልል በመግፋት ለቡድኑ ጥልቀት (depth) ሲያስገኙ ከሁለቱ የተከላካይ አማካዮች አንዱ በ late runners’ ሚና ዘግይቶ ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል በመድረስ የተፈጠረውን ክፍተት መጠቀም የሚያስችለውን ቦታ (position) ያገኛል፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት late movement (በተለይ ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል) ከ marking ነፃ ስለሚያደርግ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንም የዚህ ሲስተም ተጠቃሚ የሚሆንበትን የጨዋታ ዘይቤ እየተገበረ ያለ ይመስላል፡፡ በታክቲካዊ ዲስፕሊን የሚታወቀውን የቡድኑን አምበል ታድዮስ እና ከጎኑ የሚሰለፈው ደረጄ ሚናውን በጥሩ ሁኔታ እየተወጡ ይገኛሉ፡፡የአሰልጣኝ ፀጋዬ ቡድን በንፅፅር ከሌሎች ቡድኖች በተሻለ በመከላከል አጨዋወት (defending phase) እጅግ የተደራጀ (organized) ነው፡፡ ቡድኑ ሲከላከል ታዲዮስ በሁለቱ የመሃል ተከላካዮች (ቢንያም እና አቤል) መካከል እየገባ ጠንካራ የመከላከል መስመር ከመፍጠሩም በላይ በመስመር ተከላካዮች (አዲሱ እና አለምነህ) እና በመሃል ተከላካዮቹ መካከል ያለውን ቀዳዳ ለመድፈን ያስችላል፡፡ በዚህኛው ultra defensive አጨዋወት ለተጋጣሚ ምንም አይነት ክፍተትን ላለመስጠት ሲጥር ያየነው ቡድን በመልሶ ማጥቃት ዘይቤ ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል የሚደርስበት ፍጥነትም በመልካም የሚባል ነበር፡፡

ደረጄ መንግስቴ በንግድ ባንክ የሽግግር የጨዋታ ሒደት በተለይም በ ማጥቃት ሽግግር (attacking transition) ላይ የነበረው ሚና የጎላ ነበር፡፡ በ28ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት የመጀመርያ ግብም ለዚህ እንደ አብይ ማሳያ የምታገለገፍል ነች፡፡ ከኋለኛው መስመር ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል (በቀኝ በኩል) የተላከችውን ኳስ ዘግይቶ ቀደ ሳጥኑ በመድረስ ሊጠቀምበት ችሏል፡፡ ታዲዮስ በአብዛኛው በሜዳው አግድሞሽ (lateral movement) ሲንቀሳቀስ ደረጄ ደግሞ በሜዳው ቁመት (vertical movement) ላይ የነበረው እንቅስቃሴ ጥሩ ነበር፡፡

(ምስል 2)

22222222222

የኤሌክትሪኮች high-line defence

ይህ የመከላከል አጨዋወት ዘይቤ በተከላካዮች ፣ አማካዮች እና አጥቂዎች መካከል የሚኖረውን ክፍተት ለማጥበብ እንዲሁም በላይኛው የሜዳ ክፍል ተጋጣሚን ተጭኖ ለመጫወት ያስችላል፡፡ ተጋጣሚን በoff-side trap (ከጨዋታ ውጪ የማድረግ ስልት) ለማጥመድም አመቺ ነው፡፡ በተጋጣሚ የሜዳ ክል ብዙ ተጨዋቾችን በማጥቃት አጨዋወት ለማሳተፍም ይረዳል፡፡

ሲስተሙ በርካታ አዎንታዊ ገፅታዎችን ቢይዝም እጅግ ጠንቃቃ አቀራረብን ይጠይቃል፡፡በትክክል ካልተተገበረም አሉታዊ ጎኖቹ ዋጋ ያስከፍላሉ፡፡

ኤሌክትሪኮች ስርአቱን ሲከተሉ ለዘይቤው አስፈላጊውን ሁኔታ ያመቻቹ አይመስሉም ነበር፡፡የቀድሞ አጥቂያቸው ፊሊፕ ዳውዚ ላስቆጠራቸው ሁለት ግቦችም እንደ ምክንያት ሊጠቀስ የሚገባው ይኸው የሲስተም አተገባበር ችግር ነው፡፡

High-line defence system ለተጋጣሚ ፈጣን አጥቂዎች እና የማጥቃት አማካዮች በቀላሉ ተጋላጭ ያደርጋል፡፡በተከላካዮች መካከል የሚኖረውም የመናበብ እና የመግባባት ችሎታም ከፍተኛ ሊሆን ይገባል፡፡ኤሌክትሪኮች የዚህ ህፀፅ ተጠቂዎች ነበሩ፡፡ የመሃል ተከላካዮች የነበራቸው ፍጥነት ወደ ኋላ ተመልሰው ፊሊፕን ኳስ ማስጣል ወይም ኢላማ ማሳት የሚያስችል አልነበረም፡፡ ግብ ጠባቂው አሰግድ የተከላካዮችን ወደፊት መጠጋት ተመልክቶ ከፊቱ የነበረውን ሰፊ ክፍተት የመቀነስ አዝማምያም አልታየበትም፡፡

የአሰልጣኝ አጥናፉ ቡድን ከእረፍት መልስ በ4-2-3-1 ጨዋታውን ለማካሄድ ቢወጥንም እጅግ የተደራጀውን የንግድ ባንክ የተከላካይ ክፍል አልፎ መግባት አልቻለም፡፡ አጥቂው ፒተር ተደጋጋሚ የግብ ሙከራዎችን ከሳጥን ውጪ ያደረገበት ምክንያትም በሜዳው አግድሞሽ እጅግ ጠንክሮ (horizontal compactness) የታየውን የተከላካይ መስመር ጥሶ ማለፍ ካለመቻሉ ጋር የተያያዘ ነው፡፡

ፊሊፕ በ69ኛው እና 71ኛው ደቂቃ አከታትሎ ያስቆጠራቸው ግቦች በዚሁ የመከላከል ስርአት ላይ ካለ አናሳ ግንዛቤ የመጡ ነበሩ፡፡

ዳውዚ ፍጥነቱን ፣ የቴክኒክ ችሎታውን እና space የመጠቀም አቅሙን ተጠቅሞ ከግራ መስመር ሳጥን አካባቢ ያስቆጠራቸው ግቦች አስገራሚ ነበሩ፡፡አሰልጣኙ ይህንን ሲስተም ከመጠቀማቸው በፊት የተከላካይ መስመራቸው የተዋሃደ መስመር (coherent line) መፍጠር መቻሉን እርግጠኛ መሆን አለባቸው፡፡

(ምስል 3)

33333333333

የአብዱልከሪም Disjoint pressing

አብዱልከሪም በሊጉ ከምመለከታቸው 10 ቁጥሮች ቴክኒካዊ ችሎታን ከታክቲክ ግንዛቤ ጋር አዋህዶ የያዘ በመሆኑ ይማርከኛል፡፡ በሜዳ ውስጥ አልፎ አልፎ ደብዝዞ ቢታይም ታታሪነት እና አይደክሜ ባህርዩን አደንቅለታለሁ፡፡

በእንግሊዝ እግርኳስ ላይ የተለመደ ተጭኖ የመጫወት ዘይቤ አለ፡፡ disjoint pressing አንድ ተጫዋች ኳስ የያዘን የባላጋራ ተጫዋች ይጫናል(press) ፡፡ ሌሎቹ የቡድን አጋሮች በንቃት የኳሱን አቅጣጫ እና መድረሻ ይመለከታሉ፡፡ የአጨዋወት ስልቱ ለ10 ቁጥሮች ተስማሚ አይደለም፡፡ መጠነኛ የሆነ ‹‹ ከታክቲክ ውጪ ›› የመሆን ችግርንም ያስከትላል፡፡ በከፍተኛ ፍጥነት በሁሉም አቅጣጫ እየሮጡ መጫወት ከፍተኛ ጉልበትን ይጠይቃል፡፡ እንደ አብዱልከሪም ያሉ ባለተሰጥኦ አማካዮች ደግሞ ይህንን ሲከውኑ ሌላኛው አዎንታዊ ተፅእኖ መፍጠር የሚችል የፈጠራ ክህሎታቸውን ማየት እንዳንችል ያደርገናል፡፡ ተጫዋቹ (አብዱልከሪም) በአስፈላጊው ሰአት በወሳኝ position ላይ እንዳይገኝ ያደረገውም ይኸው ይመስለኛል፡፡ በመከላከል ላይ ባተኮረው አጨዋወቱ ከዳውዚ ይልቅ ለተከላካይ አማካዮቹ ቀርቦ መገኘቱ ዳውዚ እና የማጥቃት አማካዪቹ መካከል ያለውን ርቀት አስፍቶታል፡፡ይህም አጥቂውን ለብቻው ተነጥሎ እንዲታየን አድርጓል፡፡

(ምስል 4)

4444444444

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *