ፕሪሚየር ሊግ ፡ ሲዳማ ቡና በመሪነቱ ሲቀጥል ባንክ ወደ ላይ እየወጣ ነው

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት 3 ጨዋታዎች ትላንት እና ዛሬ ተካሂደው የደረጃ ለውጦችን አስከትለዋል፡፡

ትላንት ከፍተኛ ትኩረት አግኝቶ የነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና መከላከያ ጨዋታ ካለምንም ግብ 0-0 ተጠናቋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ የአቻ ውጤቱን ተከትሎ ለ24 ሰአታትም ቢሆን የሊጉን መሪነት ከሲዳማ ቡና ተረክቦ ቆይቷል፡፡

ዛሬ ይርጋለም ላይ በተደረገው ጨዋታ ሲዳማ ቡና አርባምንጭ ከነማን አስተናግዶ 2-0 በማሸነፍ ወደ መሪነቱ ተመልሷል፡፡ የሲዳማ ቡናን የድል ግቦች ከመረብ ያሳረፉት አንዱአለም ንጉሴ እና ኤሪክ ሙራንዳ ናቸው፡፡

በአዲስ አበባ ስታድየም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኤሌክትሪክን 3-0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ደረጃውን ወደ 3 አሳድጓል፡፡ የፀጋዬ ኪ/ማርያሙን ቡድን የድል ግቦች የቀድሞው የኤሌክትሪክ አጥቂ ፊሊፕ ዳውዚ (2) እና ደረጄ መንግስቴ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ ባንክ ሁለተኛው ዙር ከተጀመረ በኋላ ያደረጋቸውን አራቱንም ጨዋዎች በማሸነፍ ወደ መሪዎቹ መጠጋቱን ቀጥሏል፡፡

ሊጉ ነገ እና ማክሰኞ በሚደረጉ ጨዋታዎች ሲቀጥል ኢትዮጵያ ቡና ዳሽን ቢራን ፣ አዳማ ከነማ ሀዋሳ ከነማን ነገ እንዲሁም ሙገር ወልድያን ማክሰኞ ያሰተናግዳሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *