FTኢ. ቡና0-0ኢ. ኤሌክትሪክ
ጨዋታው ግብ ሳይቆጠርበት 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።
90′ ተጨማሪ ሰዐት – 4 ደቂቃ
85′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
እያሱ ታምሩ ወጥቶ ዮሴፍ ዳሙዬ ወጥቷል።
83′ አስቻለው ግርማ ከኤልያስ ማሞ በሚገርም ሁኔታ የሰጠውን ኳስ ከግብ ጠባቂው ጋር ተገናኝቶ ቢሞክርም ወደውጪ ወጥቶበታል።
80′ ሁለቱም ቡድኖች ባለፋት 10 ደቂቃዎች ወደግብ ለመድረስ ተቸግረዋል።
71′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮ ኤሌክትሪክ
አዲስ ነጋሽ (በጉዳት) ወጥቶ አቤል አክሊሉ ገብቷል።
71′ በኃይሉ ተሻገር ከሳጥኑ ውጪ የመታውን ኳስ ሃሪስተን ይዞበታል።
69′ አስቻለው ግርማ ከቅጣት ምት ወደግብ በቀጥታ የሞከረው ኳስ በግራው አግዳሚ በኩል ለጥቂት ወደውጪ ወጥቷል።
65′ አስናቀ በዳዊት እስጢፋኖስ ላይ በሰራው ጥፋት ምክንያት ቢጫ ካርድ አይቷል።
59′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
አብዱልከሪም ሐሰን ወጥቶ ኤልያስ ማሞ ገብቷል።
56 ‘ ከኢትዮጵያ ቡና የፍፁም ቅጣት ምት ክልል ግራ ጠርዝ ላይ ብሩክ አየለ የሞከራት ኳስ ወደውጪ ወጥታለች።
52′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
ያቡን ዊልያም ወጥቶ ሳዲቅ ሴቾ ገብቷል።
46′ ሁለተኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀምሯል።
የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ዋለልኝ ገብሬ እና አሸናፊ ሽብሩ ወጥተው በኃይሉ ተሻገር እና አለምነህ ግርማ ገብተዋል።
የመጀመሪያው አጋማሽ ግብ ሳይቆጠርበት በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
45′ ተጨማሪ ሰዐት – 1 ደቂቃ
36′ ጋቶች ፓኖም በድጋሚ ከሳጥኑ ውጪ ወደግብ የመታው ኳስ ከግቡ አናት በላይ ለትንሽ ወደውጪ ወጥቷል።
33′ ጋቶች ፓኖም ከመሀል ሜዳው ወደ ኤሌክትሪክ ሜዳ ጥቂት ቀረብ ብሎ በቀጥታ አክርሮ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው ሱሊማን ኤቡ አድኖበታል። ድንቅ ሙከራ !
27′ አስቻለው ግርማ በግራ መስመር ከያቡን ዊልያም የተቀበለውን ኳስ ይዞ በመግባት በቀጥታ ቢሞክርም ሱሌማን ኤቡ አድኖበታል።
23′ ኢብራሂም ፍፋኖ ከቀኝ መስመር ያሻገርለትን ግሩም ኳስ ፍፁም ገ/ማርያም ሞክሮ ሀሪስተን ሄሱ አውጥቶበታል።
19′ አዲስ ነጋሽ በ ሣህለአምላክ ተገኝ ላይ በወረደው ሸርተቴ ምክንያት የጨዋታውን የመጀመሪያ ማስጠንቂያ ካርድ ተመልክቷል።
13′ አስናቀ ሞገስ ከቅጣት ምት የተሻማውን ኳስ ከግቡ በቅርብ ርቀት ላይ ቢያገኝም ሊጠቀምበት አልቻለም።
8′ ዳዊት እስጢፋኖስ ከሳጥኑ ውጪ አክርሮ የመታውን ኳስ ሃሪስተን አውጥቶታል።
8′ ኢያሱ ታምሩ ከተከላካዮች ቀምቶ የሰጠውን ኳስ አስቻለው ሞክሮ ግብ ጠባቂው ይዞበታል።
4′ ዳዊት እስጢፋኖስ ወደግብ ያሻማውን ቅጣት ምት የኤሌክትሪክ ተጫዋቾች ሳይደርሱበት ወጥቷል።
1′ ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና አማካኝነት ተጀምሯል።
የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ለክለባቸው አምበል ጋቶች ፓኖም እና ለቀድሞ ተጫዋቻቸው ዳዊት እስጢፋኖስ የማስታወሻ ስጦታ አበርክተዋል።
የመጀመሪያ አሰላለፍ – ኢትዮ ኤሌክትሪክ
22 ሱሊማን አቡ
2 አወት ገ/ሚካኤል – 21 በረከት ተሰማ – 5 አዲስ ነጋሽ – 15 ተስፋዬ መላኩ
9 ብሩክ አየለ – 23 አሸናፊ ሽብሩ – 10 ዳዊት እስጢፋኖስ – 24 ዋለልኝ ገብሬ
16 ፍፁም ገ/ማርያም – 4 ኢብራሂም ፎፋኖ
ተጠባባቂዎች
1 ኦኛ ኦሜኛ
7 አለምነህ ግርማ
26 ሲሴ ሐሰን
11 አቤል አክሊሉ
8 በኃይሉ ተሻገር
17 አብዱልሀኪም ሱልጣን
18 ሙሉአለም ጥላሁን
የመጀመሪያ አሰላለፍ – ኢትዮጵያ ቡና
99 ሀሪሰን ሄሱ
18 ሣለአምላክ ተገኝ – 16 ኤፍሬም ወንድወሰን – 5 ወንድይፍራው ጌታሁን – 21 አስናቀ ሞገስ
17 አብዱልከሪም ሀሰን – 25 ጋቶች ፓኖም – 8 አማኑኤል ዮሐንስ
24 አስቻለው ግርማ – 28 ያቡን ዊልያም – 14 እያሱ ታምሩ
ተጠባባቂዎች
29 ዮሐንስ በዛብህ
11 ሳሙኤል ሳኑሚ
33 ፍራኦል መንግስቱ
9 ኤልያስ ማሞ
19 አክሊሉ ዋለልኝ
7 ሳዲቅ ሴቾ
27 ዮሴፍ ዳሙዬ