ደደቢት ከ አዳማ ከተማ | ቀጥታ የጽሁፍ ስርጭት

​​​FTደደቢት  0-0 አዳማ ከተማ

ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ ዳኛው በደደቢት ተጨዋቾች ተከበዋል ። ብርሀኑ ቦጋለም ቢጫ ካርድ ተመልክቷል ።

ጨዋታው ያለግብ ተጠናቋል

90+1 አክሊሉ አያነው ከማዕዘን ምት የተሻገረውን እና ግብ ጠባቂው በአግባቡ ያላራቀውን ኳስ አግኝቶ ቢሞክርም ፔንዚ በድጋሜ ይዞበታል ።

90′ ጭማሪ ደቂቃ 4 !

89 ስዩም ተስፋዬ ያሾለከለትን ኳስ ጌታነህ ከፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ቢሞክርም ተከላካዮች ተደርበው አውጥተውታል ።

87′ አልቢትሩ ዳዋ ኢቴሳን አስመስለክ ወድቀሀል በማለት የቢጫ ካርድ አሳይተውታል ። የአዳማ ደ ጋፊዎች በዳኛው ውሳኔዎች ደስተኛ አልሆኑም ።

83′ ፋሲካ አስፋው ከሳጥን ውጪ ጥሩ ኳስ ሞክሮ በግቡ አናት ወጥቶበታል ።

82′ ብሩክ ቃልቦሬ ከዳኛው ጋር በፈጠረው ሰጣ ገባ ቢጫ ካርድ ተመልክቷል ።

80′ አዳማዎች ነጥብ ይዞ ለመውጣት ወደኋላ አፈግፍገዋል ። ደደቢቶች ረካጅም ኳሶችን ተጠቅመው ጎል ለማስቆጠር እየሞከሩ ነው ። ሆኖም በተደጋጋሚ ከጫወታ ውጪ እየሆኑ ነው ።

75′ የተጨዋች ለውጥ አዳማ ከተማ

ቢንያም አየለ ገብቶ ቡልቻ ሹራ ወጥቷል ።

73′ ሳምሶን ጥላሁን ከአዳሞዎች ሳጥን ጠርዝ ላይ ጥሩ ዕድል አግኝቶ ቢሞክርም በጎን ወጥቶበታል።

70′ ከሲሳይ መውጣት በኋላ አዳማዎች ዳዋን ብቻ ከፊት በማድረግ እየተጫወቱ ነው። ደደቢቶች የቁጥር ብልጫውን የተጠቀሙበት አይመስልም ።

64′ የተጨዋች ለውጥ አዳማ ከተማ

ጥላሁን ወልዴ ሚካኤል ጆርጅን ቀይሮ ወደ ሜዳ ገብቷል ።

63 ጌታነህ ከበደ ከኤፍሬም አሻሞ የተቀበለውን ኳስ ከሳጥን ውጪ ሞክሮ ጃኮብ ፔንዚ አድኖበታል ።

59′ ቀይ ካርድ አዳማ ከተማ  ሲሳይ ቶሊ !

ሲሳይ ቶሊ ኤፍሬም አሻሞን በመጎተቱ በሁለተኛ ቢጫ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል ።

56′ ጌታነህ ከበደ ከመሀል የተላከለትን ኳስ በመጠቀም ግብ ጠባቂውን ካለፈ በኋላ ሲሞክር የግቡ ቋሚ መልሶበታል ።

55′ ከመሀል ሜዳ የተሻገረችው ኳስ የተከላካዮች ስህተት ተጨምሮበት ሚካኤል ጆርጅ ጋር ደርሳ በግንባሩ ቢሞክርም ጎል መሆን አልቻለችም ።

52′ ከአልቢትሩ ጋር በመከራከር ሚካኤል ጆርጅ ቢጫ ካርድ ተመልክቷል ።

50′ የጨዋታው ሁኔታ ከመጀመሪያው ግማሽ የተለየ አይደለም። ልዩነቱ አሁን የተመልካቹ ቁጥር መቀነሱ ነው ።

46′ ሁለተኛው አጋማሽ ተጀመረ

የተጨዋች ለውጥ አዳማ ከተማ
ተስፋይ በቀለ ወጥቶ ሞገስ ታደሰ ገብቷል

የመጀመሪያው ግማሽ ተጠናቋል !

45+3 ጌታነህ ከበደ በሽመክት ላይ የተሰራውን ጥፋት ተከትሎ የመታው ቅጣት ምት ወደ ውጪ ወጥቶበታል ።

45′ ጭማሪ ደቂቃ 2 !

43′ ጌታነህ ከበደ ከግቡ ቅርብ ርቀት ላይ ያገኘውን እድል ሳይጠቀምበት የመታት ኳስ ወደውጪ ወጥታለች ።

35′ ጨዋታው አሁንም ከተጫጫነው ድብርት አልወጣም ። ሙሉ እንቅስቃሴው በሁለቶቹ ሳጥኖች መሀል ነው ። ሁለቱም ቡድኖች ሶስተኛውን የሜዳ ክፍል መድፈር ተስኗቸዋል ።

30′ ሽመክት ጉግሳ ከግራ መስመር ያሻማውን ኳስ ኤፍሬም አሻሞ በግንባሩ ሞክሮ ለጥቂት ወደውጪ ወጥቶበታል ። የመጀመሪያ ጥሩ ሙከራ !

28′ ያልተመጠኑ ረጃጅም ኳሶች እና በርከት ያሉ የእጅ ውርወራዎች የጨዋታው ዋና ክንውኖች ሆነዋል ።

22′ ተጨዋቾች በተደጋጋሚ እየተጎዱ እየወደቁ ነው ።ግጭቶች የበረከቱበት ሙከራ አልባ ጨዋታ እየተመለከትን ነው ።

15′ ጨዋታው እጅግ ተቀዛቅዟል ። ኤፍሬም አሻሞ ቀላል ጉዳት አስተናግዶ የህክምና ውእርዳታ እየተደረገለት ነበር። ኤፍሬም ወደጨዋታው ተመልሶ ጨዋታው ቀጥሏል ።
13′ ጌታነህ ከበደ በግራ መስመር ከአዳማዎች ሳጥን ውስጥ የሞከረው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል ።

10′ ጨዋታው በደደቢቶች የኳስ ቁጥጥር እየቀጠለ ይገኛል ። አዳማዎችም በፍጥነት ወደፊት ለመሄድ እየሞከሩ ነው ።

ተጀመረ!
ጨዋታው በደደቢት አማካኝነት ተጀምሯል፡፡


የደደቢት አሰላለፍ

33 ክሌመንት አዞንቶ

7 ስዩም ተስፋዬ – 6 አይናለም ኃይለ – 14 አክሊሉ አየነው – 10 ብርሃኑ ቦጋለ

24 ካድር ኩሊባሊ – 4 አስራት መገርሳ – 8 ሳምሶን ጥላሁን

19 ሽመክት ጉግሳ – 9 ጌታነህ ከበደ – 21 ኤፍሬም አሻሞ

ተጠባባቂዎች
22 ታሪክ ጌትነት
18 አቤል እንዳለ
99 ያሬድ ብርሃኑ
15 ደስታ ደሙ
16 ሰለሞን ሐብቴ
20 የአብስራ ተስፋዬ
25 ብርሃኑ አሻሞ

የመጀመሪያ አሰላለፍ – አዳማ ከተማ

1 ጃኮብ ፔንዜ

5 ተስፋዬ በቀለ – 17 ሙጂብ ቃሲም – 4 ምኞት ደበበ – 13 ሲሳይ ቶሊ

14 ብሩክ ቃልቦሬ – 18 ፋሲካ አስፋው – 7 ሱራፌል ዳኛቸው

12 ዳዋ ሁቴሳ – 9 ሚካኤል ጆርጅ – 18 ቡልቻ ሹራ –

ተጠባባቂዎች
79 ሲሳይ ባንጫ
20 ሞገስ ታደሰ
31 ኄኖክ ካሳሁን
22 ደሳለኝ ደባሽ
15 ጥላሁን ወልዴ
23 ቢንያም አየለ
21 አዲስ ህንጻ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *