FT መከላከያ 1-0ዮንግ ስፖርትስ አ.
41′ አዲሱ ተስፋዬ
————————————————————
ተጠናቀቀ!!!!
ጨዋታው በመከላከያ 1 0 አሸናፊነት ተጠናቋል !
90′ ጭማሪ ደቂቃ 4 !
88′ ጨዋታው አሁንም የተቀዛቀዘ ሙከራ አልባ እንቅስቃሴ እያስተናገደ ይገኛል ።
85′ የተጨዋች ቅያሪ መከላከያ
ማራኪ ወርቁ ወጥቶ ታመስገን ገ/ፃዲቅ ገብቷል ።
80′ በመጀመሪያው አጋማሽ ከብዙ አማራጮች የግብ ዕድሎችን ሲፈጥሩ የነበሩት መከላከያዎች አሁን ላይ ከኋላ በረጅሙ ለአስጥቂዎች በሚላኩ ኳሶች ላይ ጥገኛ ሆነዋል ።
79′ የተጨዋች ቅያሪ መከላከያ
በሀይሉ ግርማ በ ኦጉታ ኦዶክ ተቀይሮ ከሜዳ ወጥቷል ።
78′ የተጨዋች ቅያሪ መከላከያ
ቴውድሮስ ታፈሰ በሳሙኤል ሳሊሶ ተተክቷል ።
75′ ጨዋታው በገፋ ቁጥር መከላከያዎች ወደኋላ እያፈገፈጉ ይገኛሉ ። በዚህም ምክንያት ለተጋጣሚያቸው ሰፊ የመጫወቻ ሜዳ ሰጥተዋል ።
73′ የተጨዋች ቅያሪ ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ
የመስመር አማካዩ እና የቡድኑ አንበል ንቶንብ ንጎም ሲወጣ ግሬስ ታማ ወደማዳ ገብቷል ።
69′ ዮንግ ስፖርቶች የሚሰነዝሩት ጥቃት በተደጋጋሚ ከጨዋታ ውጪ እየሆነ ይገኛል ።
65′ መከላከያዎች በተደጋጋሚ የመልሶ ማጥቃት ዕድሎችን እያገኙ ቢሆንም ከኋላ የሚነሱት ኳሶች ያልተመጠኑ በመሆናቸው እየባከኑ ይገኛሉ ።
63‘ የተጨዋች ቅያሪ ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ
የአጥቂ አማካዩ ንዶንጎ ጋሌባ ወጥቶ ሮናልድ ንጋሌ ገብቷል ።
61′ ቢጫ ካርድ !
ቴውድሮስ በቀለ በእንቅስቃሴ መሀል በሰራው ጥፋት ኳስ ወደውጪ ስትወጣ የቢጫ ካርድ ተመልክቷል ።
60′ ከመጀመሪያው አጋማሽ አንፃር ጨዋታው በመጠኑ የተቀዛቀዘ ይመስላል ። ዮንግ ስፖርቶች የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ቢወስዱም መከላከያዎች በቀኝ መስመር ያደላ መልሶ ማጥቃት እያደረጉ ነው ።
59′ አዲሱ ወደሜዳ ተመልሷል በሀይሉ ግርማም ቀለል ያለ ጉዳት ገጥሞት ወጥቶ የነበረ ቢሆንም እሱም ወደ ሜዳ ተመልሷል ።
58′ የተጨዋች ቅያሪ ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ
ጁል ዲቲች የመስመር አማካዩን ዲዮቤል ቤንዚን ተክቶ ወደሜዳ ገብቷል ።
55′ አዲሱ ተስፋዬ በደረሰበት ግጭት የህክምና እርዳታ ሊደረግለት ከሜዳ ወጥቷል ።
50′ ዮንግ ስፖርቶች ጫና ፈጥረው በመጫወት ላይ ይገኛሉ ። የጨዋታው እንቅስቃሴም ወደ መከላከያዎች ሜዳ አመዝኗል ።
48′ መከላከያዎች አሁንም በሁለት አጋጣሚዎች ያገኟቸውን የማዕዘን ምቶች ለመጠቀም ያደረጉት ጥረት መላካም የሚባል ነበር ። ግብ ባያስቆጥሩም የተጋጣሚያቸውን ተጨዋቾች ጫና ውስጥ መክተት ችለው ነበር ።
46′ ሁለተኛው አጋማሽ በመከላከያዎች አማካይነት ተጀምሯል ።
የመጀመሪያው አጋማሽ በመከላከያ 1 – 0 መሪነት ተጠናቀቀ ።
45+1 ሲያ ሳንጉ ከግራ መስመር ያሻማውን የማዕዘን ምት የመሀል ተከላካዩ ኦሊቨር ቴቼንግ በግንባሩ ቢሞክርም ኳሷ በግቡ አግዳሚ ወጥታለች ።
45′ ጭማሪ ደቂቃ 2
41 ‘ ጎል መከላከያ አዲሱ ተስፋዬ !!!!
ከቀኝ መስመር የተሻማውን የማዕዘን ምት የመሀል ተከላካዩ አዲሱ ተስፋዬ በግንባሩ በመግጨት የመጀመሪያውን ጎል አስቆጥሯል ።
39′ በግምት ከ 20 ሜትር ርቀት ላይ ሳሙኤል ሳሊሶ የሞከረው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል ።
38′ ንዶንጎ ጋሌባ ከፍፁም ቅጣት ምት ውጪ አክርሮ የሞከረው ኳስ በአቤል ማሞ ተይዞበታል ።
36′ የተሻ ግዛው በቀኝ መስመር ያሻማውን ኳስ ሳሙኤል ታዬ ከግቡ አፋፍ ላይ ቢሞክርም ግብ ጠባቂው ይዞበታል ። በጣም ለግብ የቀረበ አጋጣሚ ነበር ። ሳሙኤል ታዬ ኳሷን ባለመጠቀሙ ከፍተኛ ቁጭት ታይቶበታል ።
35′ የመሀል አማካዩ ሪቻርድ ኢቦንጉ ከሳጥን ውጪ በቀጥታ ይሞከራትን ኳስ አቤል በቀላሉ ይዞበታል ።
30′ ቀኝ መስመር ላይ ሁለት የዮንግ ስፖርትስ ተጨዋቾች ተጋጭተው ወድቀው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው ።
28′ በጨዋታው የሚደረጉ የግብ ሙከራዎች ቁጥር ቢቀንስም የጨዋታው ፍሰት ግን አሁንም ፈጠን እንዳለ ቀጥሏል። የካሜሮኑ ቡድንም እስካሁን ባለው እንቅስቃሴ ማጥቃትን መሰረት ያደረገ አጨዋወት እየተገበረ ይገኛል ።
26 ‘ ቢጫ ካርድ !
የቀኝ መስመር ተከላካዩ ኤሊቪስ ውም በሳሙኤል ሳሊሶ ላይ በሰራው ጥፋት የመጀመሪያውን ቢጫ ካርድ ተመልክቷል ።
19′ የተሻ ግዛው በግራ መስመር ይዞ የገባውን ኳስ ወደ ውስጥ ለሳሙኤል ታዬ ሲልክለት ሳሙኤል ታዬ ለ ሳሙኤል ሳሊሶ በጥሩ ሁኔታ አመቻችቶለት ሳሙኤል ሳሊሶ ከሳጥኑ ጠርዝ ላይ አክርሮ ቢሞክርም ኳስ በግቡ አናት ወጥታለች ። የሚያስቆጭ አጋጣሚ !
15′ ጨዋታው በሁለቱም ቡድኖች በኩል ቶሎ ቶሎ ወደግብ ሚደረስበት እና ሙከራዎች ሚደረጉበት ሆኖ ቀጥሏል ። እስካሁን ባለው ሁኔታ ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እየተመለከትን ነው ።
14 ‘ የቀኝ መስመር አማካዩ ዲዮቤን ቤንዚ ከመዕዘን ምት የተሻገረለትን ኳስ በእግሩ ቢሞክርም ወደላይ ወጥቶበታል ።
13′ የቀን መስመር ተከላካዩ ሽመልስ ተገኝ ከርቀት የሞከረው ኳስ በግቡ አግዳሚ ወጥቷል ።
12′ የተሻ ግዛው ሳሙኤል ሳሊሶ ከመሀል ሜዳ ያሻገረለትን ድንቅ ኳስ አገባው ተብሎ ቢጠበቅም ሙከራውን በግብ ጠባቂው ተይዞበታል ።
9′ የፊት አጥቂው ፌስተስ አሳንጎ ከተከላካዮች በረጅሙ የተላከለትን ኳስ ተጠቅሞ ከ አቤል ጋር አንድ ለአንድ ቢገናኝ ሙከራው ከኢላማ ውጪ ሆናበታለች ።
8′ ሚካኤል ደስታ ከሳሙኤል ታዬ ጋር ተቀባብሎ ከሳጥን ውስጥ የመታትንኳስ ግብ ጠባቂው ንቤሞ ሊዮፖልድ ይዞበታል ።
6′ ሳሙኤል ሳሊሶ ከረጅም ርቀት የሞከረው ኳስ በግቡ አናት ወጥቷል ።
5′ ዲዮቤን ቤንዚ በቀኝ መስመር ወደውስጥ መሬት ለመሬት ያሻገራትን ኳስ አደጋ ከመፍጠሯ በፊት አቤል ማሟ ይዟታል ።
2′ ማራኪ ወርቁ ከመሀል የተሻገረለትን ኳስ ይዞ ከተከላካዮች ጀርባ ቢገባም ሙከራ ከማድረጉ በፊት በግብ ጠብቂው ተቀድሟል ።
1’ ጨዋታው በእንግዳው ቡድን አማካይነት ጀምሯል ! መከላከያ ከቀኝ ወደግራ ዮንግ ስፖርትስ ከግራ ወደቀኝ ያጠቃሉ ።
09 ፡ 58 የክብር እንግዶች የቡድኖቹን ተጨዋቾችን እየተዋወቁ ይገኛሉ ።
የመከላከያ አሰላለፍ
1 አቤል ማሞ
2 ሽመልስ ተገኝ – 16 አዲሱ ተስፋዬ – 4 አወል አብደላህ – 3 ቴዎድሮስ በቀለ
19 ሳሙኤል ታዬ – 21 በሀይሉ ግርማ – 13 ሚካኤል ደስታ – 9 ሳሙኤል ሳሊሶ
7 ማራኪ ወርቁ – 10 የተሻ ግዛው
ተጠባባቂዎች
22 ይድነቃቸው ኪዳኔ
17 ምንተስኖት ከበደ
11 ካርሎስ ዳምጠው
15 ቴዎድሮስ ታፈሰ
26 አጉታ ኦዶክ
27 ተመስገን ገ/ፃዲቅ
28 ሚሊዮን በየነ
የዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ አሰላለፍ
30 ምቤሙ ሊዮፖልድ
18 ሚካኤል ንዶንብ – 27 ኤልቪስ ውም – 6 ኦሊቨር ቴቼንግ – 22 ብሩኖ ዮዋን
13 ሪቻርድ ኢቦንጉ – 8 ሲያ ሳንጉ
11 ዲዮቤን ቤንዚ – 7 ንዶንጎ ጋሌባ – 14 ንቶንብ ንጎም
10 ፌስተስ አሳንጎ
ተጠባባቂዎች
16 ሄርማን ሀላ
15 ሮላንድ ንጋሌ
2 አሊም ዳዎዳ
3 ጁል ዲቲች
17 ኢማኑኤል ቻይ
19 ያኒክ ዬንጋል
25 ግሬስ ታሞ
09 45 ተጨዋቾቹ ወደ መልበሻ ክፍል ገብተዋል በመቀጠል የሁለቱን ቡድኖች አሰላለፍ ይዘን እንመለሳለን ።
09 ፡ 30 የሁለቱ ቡድኖች ተጨዋቾች ሰነታቸውን እያሟሟቁ ይገኛሉ ።
ባለፉት አራት አመታት ውስጥ ሶስት ጊዜ በዚህ የሀጉሪቱ ውድድር ላይ መሳተፍ የቻለው መከላከያ ባለፉት ሁለት አመታት በ ኬንያው ኤ ኤፍ ሲ ሊኦፓርድስ 4 – 1 እንዲሁም በግብፁ ምስር አል ማቃሳ 6 – 1 በሆኑ አጠቃላይ ውጤቶች በመሸነፍ በመጀመሪያው ዙር ከውድድሩ መሰናበቱ ይታወሳል ። ክለቡ በአምናው የኢትዮጵያ ዋንጫ ላይ ለፍፃሜ በመድረሱም በዘንድሮው የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ውድድር ላይ ኢትዮጵያን በመወከል የመሳተፍ ዕድሉን አግኝቷል ።
የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ካሜሮን ክለብ የሆነው ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ 2004 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር ላይም ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈው በ 2014 ዓ.ም ነበር። ክለቡ አምና በሀገሪቱ የሊግ ውድድር ሁለተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ዘንድሮም በሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ። ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ የመጨረሻዎቹን ሶስት የሊግ ጨዋታዎቹን ማሸነፍ ችሏል ።
ሠላም ውድ አንባቢዎቻችን !
ዛሬ 10 ሰዐት ላይ በሚጀምረው ጨዋታ የኢትዮጵያው መከላከያ ከካሜሮኑ ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ ጋር የሚያደርገውን የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታ ከአዲስ አበባ ስታድየም በመሆን ልናስነብባቸሁ ተዘጋጅተናል ።
መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር !