የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ አጫጭር ዜናዎች

ሀድያ ሆሳዕና ቅጣት ተጣለበት

ሀድያ ሆሳዕና በሜዳው ባደረገው ጨዋታ ደጋፊዎች ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጪ የሆነ አድራጎት በመፈፀማቸው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን ኮሚቴ 2 የሜዳው ጨዋታዎችን ከሜዳው ውጪ እንዲያደርግ እነና 50,000 ብር እንዲከፍል ቅጣት ተላልፎበታል፡፡

ቅጣቱን ተከትሎ በ13ኛው ሳምንት እሁድ ሀዲያ ሆሳዕና ከ ደቡብ ፖሊስ የሚያደርጉት ጨዋታ ቡታጅራ ላይ ይደረጋል፡፡

የተስተካካይ ጨዋታዎች መርሃ ግብር ይፋ ሆኗል

በተለያዩ ምክንያቶች ሳይካሄዱ የቀሩ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎች መቼ እንደሚደረጉ የሊግ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡ የተስተካካይ ጨዋታዎች ፕሮግራም ይህንን ይመስላል፡-

አርብ መጋቢት 1 ቀን 2009

09:00 ጂንካ ከተማ ከ ስልጤ ወራቤ (ጂንካ)

09:00 ዲላ ከተማ ከ ድሬዳዋ ፖሊስ (ዲላ)

09:00 ሀላባ ከተማ ከ ጅማ ከተማ (ሀላባ)

ቅዳሜ መጋቢት 2 ቀን 2009

09:00 ሽረ እንዳስላሴ ከ ባህርዳር ከተማ (ሽረ)

ሀሙስ መጋቢት 7 ቀን 2009

09:00 ነቀምት ከተማ ከ ሀላባ ከተማ (ነቀምት)

09:00 ስልጤ ወራቤ ከ ነገሌ ቦረና (ወራቤ)

በጥሎ ማለፉ ሽረ እንዳስላሴ ብቻ ይሳተፋል

በ2009 ኢትዮጵያ ጥለሎ ማለፍ 5 የከፍተኛ ክለቦች በድልድሉ ውስጥ ቢካተቱም 4 ክለቦች በተለያየ ምክንያት ከውድድሩ ራሳቸውን አግልለዋል፡፡ በውድድሩ ላይ የቀረው ብቸኛ ክለብም ሽረ እንዳስላሴ ብቻ ሆኗል፡፡ ሽረ ነገ አአ ስታድየም ላይ በ11:30 ኢትዮ ኤሌክትሪክን የሚገጥም ይሆናል፡፡

የ1ኛ ዙር ግምገማ መጋቢት 3 ይካሄዳል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ1ኛ ዙር ግምገማ መጋቢት 3 እንደሚካሄድ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡ የት እንደሚካሄድ ግን የታወቀ ነገር የለም፡፡

የ2ኛ ዙር የሚጀመርበት ቀን ታውቋል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 1ኛ ዙር መደበኛ ጨዋታዎች የካቲት 26 ሲጠናቀቁ ተስተካካይ ጨዋታዎች እስከ መጋቢት 7 ድረስ ይዘልቃሉ፡፡ በፌዴሬሽኑ መርሃ ግብር መሰረት የሁለተኛው ዙር ውድድር የሚጀምረው መጋቢት 10 ቀን 2009 ነው፡፡

የ13ኛ ሳምንት ጨዋታዎች እሁድ ይደረጋሉ

የከፍተኛ ሊጉ 13ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ይካሄዳሉ፡፡ ውድድሮቹን ለመከታተል እንዲያመቻችሁ መርሃ ግብሮቹ እነዚህን ይመስላሉ፡፡

(ስማቸው ቅድሚያ የተፃፉት ባለሜዳ ናቸው፡፡ የሀድያ ሆሳዕና እና ደቡብ ፖሊስ ጨዋታ ቡታጅራ ይደረጋል)

ምድብ ሀ

[table id=194/]

[league_table 18186]

ምድብ ለ

[table id=195/]

[league_table 18205]

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *