ፌዴሬሽኑ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ አድርጎ መርጧል

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከቴክኒክ ኮሚቴው የቀረበለትን ሀሳብ በማጽደቅ የአዳማ ከተማው አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን የብሄራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ በዛሬው እለት መምረጡን ሶከር ኢትዮጵያ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮቿ አረጋግጣለች፡፡

የፌዴሬሽኑ ቴክኒክ ኮሚቴ ለብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነት የወጣውን የቅጥር ማስታወቂያ ተከትሎ ማስረጃቸውን ያስገቡ አሰልጣኞችና  በመመልከት አሰልጣኝ አሸናፊን በከፍተኛ ድመፅ በመምረጥ ለፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ማስተላለፉ የሚታወስ ነው፡፡ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴውም በዛሬው እለት በኃይሌ ሪዞርት ባደረገው ድንገተኛ ስብሰባ የአሰልጣኝ አሸናፊን አሰልጣኝነት አጽድቋል፡፡ በመጪዎቹ ጊዜያትም ዝርዝር የኮንትራት ድርድሮች በፌዴሬሽኑ እና በአሰልጣኙ መካከል ተደርገው የአሰልጣኝ አሸናፊ ሹመት ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *