ፕሪሚየር ሊግ – ሙገር ከፕሪሚር ሊጉ ተሰናብቷል

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎች ሙገር ሲሚንቶ ወደ ብሄራዊ ሊግ መውረዱን ሲያረጋግጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ በደማቅ ፕሮግራም ዋንጫውን ተረክቧል፡፡

በአዲስ አበባ ስታድየም 8፡00 ላይ መከላከያን የገጠመው ሙገር ሲሚንቶ በበረከት ሳሙኤል ግብ 1-0 ቢያሸንፍም ኤሌክትሪክ ወላይታ ድቻን በተመሳሳይ 1-0 በማሸነፉ የአሰላው ቡድን በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ብሄራዊ ሊግ ወርዷል፡፡

ከጨዋታው ፍፃሜ በኋላ የሙገር ተጫዋቾች በስታድየሙ በተሰራጨው የተሳሳተ መረጃ ኤሌክትሪክ እንደተሸነፈ በማመን ደስታቸውን ሲገልፁ ተስተውለዋል፡፡

DSC01623

በ1986 ዓ.ም የተመሰረተው ሙገር ሲሚንቶ ስፖርት ክለብ በ1991 ቅዱስ ጊዮርጊስን ተከትሎ ከብሀራዊ ሊግ ካደገ ወዲህ ለአመታት በደረጃ ሰንጠረዡ ወገብ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ቢቆይም ሳላዲን ሰኢድ እና አንዱአለም ንጉሴ የመሳሰሉ ኮከቦችን ለኢትዮጵያ እግርኳስ በማበርከት የሚታወቅ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *