የብሄራዊ ቡድኑ የምርጫ ጨዋታ ሁለተኛ ቀን…

ትላንትና ጠዋት ዝግጅት የጀመረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 23 ተጫዋቾችን ለመለየት ዛሬም የእርስ በእርስ ጨዋታ አድርጓል፡፡

የእርስ በእርስ ጨዋታው ትላንት እንደተደረገው ሁሉ በ4 ቡድኖች የተከፈለ ሲሆን ሁለት ቡድኖች እያንዳንዳቸው 11 ተጫዋቾችን አቅፈዋል፡፡ አንድ ቡድን 10 ቀሪው ደግሞ 9 ተጨዋቾችን ይዘው ጨዋታቸውን አከናውነዋል፡፡

በቅድሚያ የተጫወቱት ቢጫ መለያ የለበሱ እና ቢጫ/አረንጓዴ የለበሱ ሲሆኑ ከትላንትናው የተወሰኑ ለውጦች ተደርገዋል፡፡ በአረንጓዴ/ቢጫ በኩል ትላንት የተጫወተው ሙሉአለም ጥላሁን አርፎ 45 ደቂቃ ተጫውቶ የነበረው ስዩም ተስፋዬ ሲገባ በአቤል ማሞ ምትክ ደግሞ ታሪክ ጌትነት ተጫውተዋል፡፡

በሁለቱ በኩል የተሰለፉት ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው

ቢጫ – ታሪክ ጌትነት – ታጋይ አበበ – አዲሱ ተስፋዬ – ሙጂብ ቃሲም – ቴዎድሮስ በቀለ – ጋቶች ፓኖም – ሳምሶን ጥላሁን – በኃይሉ አሰፋ – ራምኬል ሎክ – አላዛር ፋሲካ – በረከት ይስሃቅ

አረንጓዴ/ቢጫ – ጀማል ጣሰው – ተካልኝ ደጀኔ – አስቻለው ታመነ – ሳላዲን በርጊቾ – ስዩም ተስፋዬ – አሸናፊ ሽብሩ – አስቻለው ግርማ – ሱራፌል ጌታቸው – ታፈሰ ሰለሞን – ኤፍሬም አሻሞ – ዮናታን ከበደ

ጨዋታው በአቻ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን በረከት ይስሃቅ (4’) እና በኃይሉ አሰፋ (43’) ለቢጫ ፣ ኤፍሬም አሻሞ (10’) እና ሱራፌል ጌታቸው (39’) ለአረንጓዴ/ቢጫ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡

new

በ2ኛው ጨዋታ ቢጫ እና አረንጓዴ መለያ የለበሱ ቡድኖች የተጫወቱ ሲሆን ጀማል እና ታሪክ በድጋሚ ለ45 ደቂቃዎች ያህል ተጫውተዋል፡፡ ቢጫ ለባሾቹ ትናንት አስራት መገርሳ በጉዳት በመውጣቱ ዛሬ በ9 ተጫዋቾች ለመጫወት ሲገደዱ አረንጓዴዎቹ በ10 ተጫዋች ተጫውተዋል::

በሁለቱ በኩል የተሰለፉት ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው፡፡

አረንጓዴ መለያ – አቤል ማሞ – ዘካርያስ ቱጂ – ኤፍሬም ወንድወሰን – ሞገስ ታደሰ – ሲሳይ ቶሊ – ታከለ አለማየሁ – ፍሬው ሰለሞን – ኤፍሬም ቀሬ – ብሩክ ቃልቦሬ – ተመስገን ተክሌ

ቢጫ መለያ – ጀማል ጣሰው – ግርማ በቀለ – ተስፋዬ በቀለ – በረከት ቦጋለ – ጋዲሳ መብራቴ – ምንተስኖት አዳነ – ባዬ ገዛኸኝ – ታደለ መንገሻ – ቢንያም አሰፋ

ጨዋታው በጎዶሎ ተጫዋቾች በተጫወቱት ቢጫ ለባሾች 3-1 አሸናፊነት ሲጠናቀቅ ጋዲሳ መብራቴ (57’) ፣ ባዬ ገዛኸኝ (57’) እና ምንተስኖት አዳነ (80’) ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡ የአረንጓዴዎቹን ግብ ደግሞ ብሩክ ቃልቦሬ (19’) አስቆጥሯል፡፡

በእረፍት ሰአት ላይ ታሪክ ጌትነት ጀማል ጣሰውን ተክቶ 2ኛው አጋማሽን የተጫወተ ሲሆን በአጠቃላይ በዛሬው እለት 40 ተጫዋቾች በምርጫ ጨዋታው ላይ ተሳትፈዋል፡፡

ትናንት የተጫወተው ሙሉአለም ጥላሁን እና በትናንቱ ጨዋታ በ53ኛው ደቂቃ ጨዋታውን አቋርጦ የወጣው አስራት መገርሳ የዛሬው ጨዋታ ሲያልፋቸው ለአለም ብርሃኑ እና አብዱልከሪም መሃመድ በጉዳት ምክንያት ሁለቱንም ቀናት አልተሳተፉም፡፡

አሰልጣን ዮሃንስ ሳህሌ ባስታወቁት መሰረት ትናንት እና ዛሬ 4 ጨዋታዎች አድርገው የተጫዋቾቹን አቋም የተመለከቱ ሲሆን ዛሬ አመሻሽ ላይ የመጨረሻው 23 ተጫዋቾች ዝርዝር ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *