የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነር ጃንዛ ዛሬ ቡድናቸው በወዳጅነት ጨዋታ ዋልያዎቹን 1-0 ካሸነፈ በኋላ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ አሰልጣኙ የሰጡት አስተያየት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
‹‹ ኢትዮጵያ የወዳጅነት ጨዋታውን ከኛ ጋር ስላደረገች እናመሰግናለን፡፡ በኢትዮጵያ እና ዛምቢያ መካከል ቀላል የሚባል ጨዋታ እንደሌለ መናገር እፈልጋለሁ፡፡ በ2013 የአፍሪካ ዋንጫ ከኛ ጋር በአንድ ምድብ ውስጥ ከነበረችው ኢትዮጵያ ጋር ቀላል ፉክክር እንደማይገጥመን እናውቃለን፡፡ የኛ ተጫዋቾች ግብ ለማስቆጠር ታግለዋል፡፡
‹‹ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከፊታችን ስለሚጠብቀን ጠንካራ ጨዋታ ከናንተ ጋር በማድረጋችን ደስተኞች ነን፡፡ ከጨዋታው መጥፎ ውጤት እናገኝ ይሆን ብለን አልፈራንም፡፡ ምክንያቱም ቡድናችን ገና አዲስ እና በመገንባት ላይ ያለ ቡድን ነው፡፡ ጨዋታው ለኛ ጥሩ ልምድ ሰጥቶናል፡፡ ከጨዋታው በርካታ ጥሩ ነገሮች አይተን ወጥተናል፡፡
‹‹ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ብዙ ጠንካራ ገኖች አሉት፡፡ ወደ ፊት የመሄድና ግብ የማስቆጠር ጉጉት አላቸው ፡፡ ነገር ግን በማጥቃት ወረዳው ላይ ያላቸውን ብቃት እና እድሎችን ወደ ግብ መቀየር ላይ ማሻሻል ይጠበቅባቸዋል፡፡ ››