የብሄራዊ ቡድኑ የማበረታቻ ሽልማት

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ብሄራዊ ቡድኑ በአፍሪካ ዋንጫ እና ቻን ማጣሪያ ላስመዘገበው ውጤት የማበረታቻ ሽልማት አበርክቷል ፡፡ ዛሬ 12፡00 ላይ በካፒተል ሆቴል እና ስፓ በተካሄደው ስነ-ስርአት ለተጫዋቾች ፣ የአሰልጣኝ ቡድኑ እና አጠቃላይ የልኡካን ቡድን አባላት የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ጁነይዲ ባሻ በስነስርአቱ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር የብሄራዊ ቡድኑ ጉዞ በድል ቢጀመርም ፍፃሜው እንዲያምር ገና ብዙ የሚሰሩ ስራዎች እንደሚቀሩ ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም በብሄራዊ ቡድኑ ዙርያ የሚገኙ አካላት እና የሚድያ ሰዎች ለዋልያዎቹ ያላቸውን ድጋፍ እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡

በዛሬው የሽልማት ስነስርአት ላይ የተበረከቱት ሽልማቶች በሚከተለው መልኩ ተከናውነዋል፡-

-ከ90 ደቂቃ በላይ የተጫወቱ – 20,000
-ከ90 ደቂቃ በታች የተጫወቱ – 15,000
-ከ45 ደቂቃ በታች የተጫወቱ – 10,000
-ምንም ጨዋታ ያላደረጉ (ጀማል ጣሰውን ጨምሮ) – 7,000
-ዮሃንስ ሳህሌ – ዋና አሰልጣኝ – 25,000
-ፋሲል ተካልኝ – ረዳት አሰልጣኝ – 15,000
-አሊ ረዲ – የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ – 10,000
-ዮሴፍ ተስፋዬ – የቡድን መሪ – 10,000
-ዶ/ር አያሌው ጥላሁን – ሀኪም – 7,000
-በኃይሉ አበራ – ወጌሻ – 6,000
-ዳንኤል ዘርአብሩክ – ትጥቅ ያዥ – 2,000
-ዘውዱ ፋንታዬ – ሾፌር – 2,000

* ውጪ ሃገራት ለሚጫወቱ ተጫዋቾች በአድራሻቸው ይላክላቸዋል

* የቡድን መሪው አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ ለ37ቱ የልኡካን ቡድን አባላት ለእያንዳንዳቸው የ 1,000 ብር ሽልማት አበርክተዋል ፡፡