ኢትዮጵያዊው አማካይ ሽመልስ በቀለ ማክሰኞ ምሽት በተደረገ የግብፅ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ክለቡ ፔትሮጀት በአል አሃሊ በተሸነፈበት ጨዋታ ግብ አስቆጥሯል፡፡ በስዊዝ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሽመልስ በቀለ በስምንተኛው ደቂቃ ግብ ማስቆጠር ችሏል፡፡ ሽመልስ ለፔትሮጀት ሁለተኛ ግብ ማስቆጠር የሚችልበትን አጋጣሚ አግኝቶ የነበረ ቢሆንም የአሃሊው ግብ ጠባቂ አህመድ አድል አምክኗታል፡፡ ጨዋታውን አል አሃሊ በዋሊድ ሱሌማን እና በፔትሮጀቱ ተጨዋች አህመድ መግዲ በራሱ ግብ ላይ ባስቆጠራት ግብ 2ለ1 ማሸነፍ ችሏል፡፡ ሽመልስ በውድድር ዘመኑ ያስቆጠረውን ግብ መጠን ወደ ስምንት ሲያደርስ በግብፅ ፕሪምየር ሊግ እያሳየ በሚገኘው አቋም የአንዳንድ ክለቦችን ቀልብ እየሳበ ነው፡፡ በቅርቡ የግብፁ ክለብ ኢ.ኤን.ፒ.ፒ.አይ የሽመልስ ፈላጊ መሆኑ መነገሩ የሚታወስ ነው፡፡
የሽመልስ በቀለ ጎል ለማየት ይህንነ ሊንክ ይከተሉ፡፡
https://youtu.be/jmfbrnJOIPI