ቅዱስ ጊዮርጊስ የሳላዲን ሰኢድን ውል አድሷል  

ለአራት ተከታታይ አመት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ማሸነፍ የቻለው እና በቀጣይ አመት በፕሪምየር ሊጉ እና በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊጉ ተፎካካሪ ለመሆን የተለያዩ ተጨዋቾችን በማስፈረም እንዲሁም ውላቸው ያለቀ ተጨዋቾችን ውል በማደስ ላይ የሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ የፊት መስመር አጥቂውን ሳላዲን ሰኢድንም ውል አድሷል፡፡

ሰኔ 30 ኮንትራቱ የተጠናቀቀው ሳላዲን ሰኢድ ስሙ ከተለያዩ የግብፅ ክለቦች ጋር ተያይዞ ሲዘገብ የቆየ ሲሆን ተጨዋቹ በተለይ ወደ ግብፅ አምርቶ ከአል ማስሪ ጋር ድርድሮችን ያደረገ ቢሆንም ሁለቱ ክለቦች ስምምነት ላይ ሳይደርሱ ቀርተዋል፡፡

ፈረሰኞቹ ተጨዋቹን ለሁለት አመት በቡድናቸው ለማቆየት የተስማሙ ሲሆን ተጨዋቹ በተለይ በዚኛው አመት ካሳየው የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ብቃት እንዲሁም ካስቆጠራቸው ጎሎች(7 ቻምፒየንስ ሊግ፣15 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ)አንፃር በቀጣይ ቡድኑን ይጠቅማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከዚህ በፊት ለአለም ብርሃኑ፣አብዱልከሪም መሃመድ ፣፡ሙሉአለም መስፍን ፣ ጋዲሳ መብራቴ ፣ ታደለ መንገሻ እንዲሁም አሜ መሐመድን ወደ ክለባቸው መቀላቀል የቻሉ ሲሆን አስቻለው ታመነ ፣ ሳላዲን በርጌቾ ፣ ደጉ ደበበ እና ናትናኤል ዘለቀ ለሁለት አመት ፤ አበባው ቡጣቆ እና በኃይሉ አሰፋ ለአንድ አመት ውላቸውን ማራዘማቸው የሚታወሰ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *