ሙሉአለም ጥላሁን ወደ ወልዋሎ አምርቷል 

ከከፍተኛ ሊጉ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደግ የቻለው ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ ቡድኑን በአዳዲስ ተጨዋቾች መሙላቱን ቀጥሎ ሙሉአለም ጥላሁንን አስፈርሟል፡፡

የቀድሞው የኢትዮጵያ መድን፣ ኢትዮጵያ ቡና እና መከላከያ አጥቂ ሙሉአለም የተጠናቀቀውን የውድድር አመት በኢትዮ ኤሌክትሪክ ያሳለፈ ሲሆን አመቱን አብረው ያሳለፉት በረከት ተሰማ ፣ ዋለልኝ ገብሬ እና ብሩክ አየለን ተከትሎ ወደ አዲግራቱ ክለብ አምርቷል፡፡

ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ ከሙሉአለም በፊት በረከት ተሰማ፣ዋለልኝ ገብሬ፣ብሩክ አየለ፣እንየው ካሳሁን ፣እዮብ ወ/ምርያም፣ወግደረስ ታዬ፣ተስፋዬ ዲባባ፣ቢንያም አየለ፣ዘውዱ መስፍን ፣ሮቤል ግርማ ያስፈረሙ ሲሆን የ12 ተጨዋቾችንም ውል ማደሳቸው ይታወሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *