ዳዊት ፍቃዱ ወደ ሀዋሳ ከተማ አምርቷል

ያለፉትን ወራት ከደደቢት ጋር ውዝግብ ውስጥ ቆይቶ የነበረው ዳዊት ፍቃዱ በፌዴሬሽኑ መልቀቂያ እንዲሰጠው በመወሰን ወደፈለገበት እንዲሄድ መፍቀዱ የሚታወስ ነው፡፡ ይህንን ተከትሎም ወደ ሀዋሳ ከተማ ማምራቱ እርግጥ ሆኗል፡፡ በክለቡም ለአንድ የውድድር ዘመን ለመጫወት ተስማምቷል፡፡

ከ2002 ኢትዮጵያ ቡናን ለቆ ወደ ደደቢት ያመራውና ከክለቡ ጋር የፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ያነሳው ዳዊት በዘንድሮው የውድድር ዘመን ከጉዳት እና ከክለቡ ጋር በገባው ቅራኔ ምክንያት እምባዛም የመጫወት እድል ሳያገኝ ቀርቷል፡፡

ሀዋሳ ከተማ የቡድኑ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ ያጠናቀቀው ጃኮ አራፋትን በማጣቱ ዳዊት ቡድኑን ከተቀላቀሉት ሌሎች አጥቂዎች (ያቡን ዊልያም እና ሳዲቅ ሴቾ) ጋር የአጥቂ መስመር ክፍተቱን እንደሚደፍን ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *