ያሬድ ዘውድነህ ወደ ድሬዳዋ ተመልሷል

ያሬድ ዘውድነህ ከወልዲያ ጋር ያለውን ውል አፍርሶ ለድሬዳዋ ከተማ ፊርማውን አኑሯል፡፡

በውድድር አመቱ መጀመርያ የፈረሰው ዳሽን ቢራን ለቆ ወደ ወልዲያ ያመራው የመሀል ተከላካዩ ያሬድ በክለቡ መልካም ጊዜ ማሳለፍ የቻለ ሲሆን ቀሪ የአንድ አመት ውል ቢቀረውም በስምምነት የውል ማፍረሻውን 120 ሺህ ብር ከፍሎ በመለያየት ወደ ትውልድ ከተማው ተመልሶ ለድሬዳዋ ከተማ ፈርሟል፡፡

በዝውውር መስኮቱ የመጀመርያ ቀናት በርካታ ተጫዋቾችን በማስፈረም ኋላ ላይ የተቀዛቀዘው ድሬዳዋ ከተማ ከያሬድ በፊት 11 ተጫዋቾችን ማስፈረሙ ይታወሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *