ሙሉአለም ረጋሳ በቅርቡ ለሀዋሳ ከተማ እንደሚፈርም ይጠበቃል

የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የብሔራዊ ቡድን ድንቅ አማካይ ሙሉአለም ረጋሳ የሙከራ ጊዜ እያሳለፈበት በሚገኘው ሀዋሳ ከተማ ኮንትራት ሊቀርብለት መቃረቡ ታውቋል፡፡ ክለቡም ሙሉአለምን ለማስፈረም እንደተዘጋጀ ፍንጭ ሰጥቷል፡፡

በሙሉአለም ረጋሳ የሙከራ ጊዜ እና ቀጣይ ሁኔታ ዙርያ ለሶከር ኢትዮጵያ አስተያየቱን የሰጠው የሀዋሳ ከተማ ምክትል አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት እስካሁን ባለው የሙከራ ጊዜ በጨዋታም ሆነ በልምምድ ወቅት እያሳየ ባለው እንቅስቃሴ የክለቡ አሰልጣኞችም ሆኑ ተጨዋቾች ደስተኛ እንደሆኑና ያለውን እንቅስቃሴ ይዞ መቀጠል የሚችል ከሆነ ለሀዋሳ ከነማ ሊፈርም እንደሚችል ተናግረዋል።

በ1990ዎቹ ብዙዎቹን ከሚያስማሙ የተዋጣላቸው አማካዮች መካከል አንዱ የነበረው ሙሉአለም ረጋሳ ከ11 አመታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ዋናው ቡድን ቆይታ በኋላ በ2000 ከክለቡ ጋር ተለያይቶ ለሰበታ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን የተጫወተ ሲሆን ያለፉትን ሁለት አመታት ክለብ አልባ ሆኖ መቆየቱን ተከትሎ እግር ኳስ መጫወት አቁሟል ቢባልም ሀዋሳ ከተማ የሙከራ እድል ሰጥቶት ክረምቱን በክለቡ እያሳለፈ ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *