ኢትዮጵያ ከ ኬንያ፡ ከ20 አመት በታች ሴቶች አለም ዋንጫ ማጣርያ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ተጠናቀቀ ኢትዮጵያ 2-2 ኬንያ

22′ ምርቃት ፈለቀ 29′ አለምነሽ ገረመው | 89′ ሎራዞኒ ቪቪያን 90+3′ ራቻኤሊ ኦቶሮ


ተጠናቀቀ!!!

ጨዋታው 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቀቀ፡፡ ኢትዮጵያ በመጀመርያው አጋማሽ የያዘችውን መሪነት ማስጠበቅ ሳትችል ስትቀር ኬንያ ወሳኝ የሜዳ ውጪ ውጤት ይዛ ወጥታለች፡፡

ጎልልል ኬንያ
90+3′ ከመስመር የተሻማውን ኳስ ራቻኤሊ ኦቶሮ በግምባሯ በመግጨት አስቆጥራ ኬንያን አቻ አደረገች፡፡

90+2′ ኬንያዎች አቻ ለመሆን ጫና ፈጥረው መጫወት ጀምረዋል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
90′ ሴናፍ ዋቁማ ወጥታ ብሩክታዊት አየለ ገብታለች፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 4

ጎልልል ኬኒያ

89′ ሎራዞኒ ቪቪያን ፍ/ቅጣት ምቱን በአግባቡ ተጠቅማ የኬንያን ወሳኝ የሜዳ ውጪ ግብ አስቆጥራለች፡፡

ፍፁም ቅጣት ምት!

88′ ቅድስት ዘለቀ ፍ/ቅጣት ክልል ውስጥ በሰራችሁ ጥፋት ዳኛዋ ፍ/ቅጣት ምት ሰታለች፡፡

86′ ትዕግስት አበራ ኬንያዎች አልፎ አልፎ ወደ ግብ የሚመቷቸውን ጠንካራ ምቶች በመመለስ ከተመልካቹ አድናቆት ተችሯታል፡፡

78′ ጨዋታው ተመጣጣኝ የሆነ ፍክክር አእየታየበት ሲሆን መጠነኛ ዝናብም መጣል ጀምሯል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኬንያ
76′ ማርታ አውቶሊቲ ወጥታ ቶስካህ ሀሳቪይቪንዳ ገብታለች፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
69′ ሜላት ደመቀ ወጥታ ዘይነባ ሰይድ ተክታት ገብታለች ፡፡

63′ ሴናፍ ዋቁማ ከምርቃት ፈለቀ ያገኘችውን ኳስ ግብ ጠባቂዋን አልፋ አስቆጠረች ሲባል ወደ ላይ ሰዳዋለች፡፡

የተጫዋቾች ለውጥ – ኢትዮጵያ
61′ የምስራች ላቀው ወጥታ ጤናዬ ወመሴ ገብታለች፡፡

ቢጫ ካርድ

60′ ዊኬቴ ካሪ ምርቃት ፈለቀ ላይ በሰራችው ጥፋት የጨዋታውን የመጀመርያ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክታለች፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኬንያ

57′ ጄትሪክስ ሽካንግዋ ወጥታ ዲያና ዋቼራ ገብታለች

49′ አለምነሽ ገረመው ከመሀል ሜዳ አቅራቢያ የግብ ጠባቂዋን መውጣት ተመልክታ የመታችው ኳስ እንደምንም ወጥቶባታል፡፡ ወጣቶቹ ሉሲዎች መልካም የሚባል እንቅስቃሴን እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ተጀመረ

ሁለተኛው አጋማሽ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አማካኝነት ተጀምሯል፡፡


እረፍት

የመጀመርያው አጋማሽ በኢትዮጵያ መሪነት ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ -2

42′ ሴናፍ ዋቁማ ከምርቃት ፈለቀ የተሰጣትን ኳስ ከርቀት መትታ ሊሊያን አዎር እንደምንም ተወርውራ አውጥታዋለች፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኬንያ

40′ ሜሪ ኤዮ ወጥታ ራቻኤሊ ኦትሮ ገብታለች፡፡ ኬንያዎች ወደ ጨዋታው ለመመለስ ተጨማሪ አጥቂ አስገብተዋል፡፡

35′ ኬንያዎች ያገኙትን የማዕዘን ምት ሺሊዋትሶ በግንባሯ ገጭታ የቀኝ ቋሚውን ታኮ ወጥቷል፡፡

ጎልልል!!! ኢትዮጵያ
29′ አለምነሽ ገረመው በግል ጥረቷ ሁለት ተጫዋቾችን አልፋ በግምት ከ25 ሜትር ርቀት አክርራ ግብ አስቆጥራ የኢትዮጵያን መሪነት ወደ ሁለት ከፍ አድርጋለች፡፡

ጎልልል!!! ኢትዮጵያ

22′ ቤተልሄም ከፍያለው በረጅሙ ያሻገረችውን ኳስ ምርቃት ፈለቀ በአግባቡ ተቆጣጥራ ወደ ግብነት በመቀየር ኢትዮጽያን መሪ አድርጋለች፡፡

17′ ቤተልሄም ከፍያለው ከቀኝ መስመር በእጅ ውርወራ ያሻገረችውን ምርቃን ፈለቀ በግንባሩዋ ገጭታ አምክናለች፡፡ ምናባትም ኢትዮጵያ መሪ ምትሆንበት አጋጣሚም ነበር፡፡

13′ አምበሏ የምስራች ላቀው ከርቀት የመታችውን ኳስ ግብ ጠባቂዋ ሊሊያን አዎር ይዛባታለች

8′ አጥቂዋ ማርታ አውቶሊቲ በሳጥን ውስጥ ገብታ ወደ ግብ የመታችውን ኳስ አረጋሽ ፀጋዬ እንደምንም ተደርባ አውጥታዋለች፡፡

5′ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ፈጣን እንቅስቃሴ ቢያደርግም የኬንያን የተከላካይ መስመር ሰብሮ መግባት አልቻቸም፡፡

ተጀመረ!

ጨዋታው በኬንያ ብሔራዊ ቡድን አማካኝነት ተጀምሯል ፡፡

9:50 የሁለቱም ሀገራት ብሔራዊ መዝሙር እየተዘመረ ይገኛል፡፡

9:47 የሁለቱም ሀገራት ተጫዋቾች ወደ ሜዳ ገብተው የእለቱ የክብር እንግዶችን በመተዋወቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

9:41 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ጁነይዲ ባሻ እና ስራ አስፈፃሚዎችን ጨምሮ የኬንያ የፌድሬሽን አመራሮችም ተገኝተዋል፡፡

አሰላለፍ – ኢትዮጵያ
12 ትዕግስት አበራ – 5 ቅድስት ዘለቀ – 2 አረጋሽ ፀጋዬ – 3 ባንቻአየሁ ታደሰ – 4 ቤተልሄም ከፍያለው – 10 እመቤት አዲሱ – 8 ሜላት ደመቀ — 11 የምስራች ላቀው – 7 አለምነሽ ገረመው – 9 ምርቃት ፈለቀ – 6 ሴናፍ ዋቁማ

ተጠባባቂዎች
1 እምወድሽ ይርጋሸዋ – 15 ምህረት መለሰ – 13 ፅዮን ፈየራ – 16 ብሩክታዊት አየለ – 18 ዘይነባ ሰይድ – 17 ጤናዬ ወሜሴ – 14 ትመር ጠንክር

አሰላለፍ – ኬንያ
1 ሊሊያን አዎር – 15 ዊኬቴ ካሪ – 2 ማውሬይ ካቢካስ – 4 ቪቪያን ማካዲካ – 14 ሉሲ አኮቴ – 13 ሼሪክ አንጌሀ – 7 ሜሪ ኤዮ – 17 ሎራዞኒ ቪቪያን – 12 ማርታ አሙቶሊቲ – 10 ሲንያዘን ሺሊዋትሶ – 11ጄትሪክስ ሽካንግዋ

ተጠባባቂዎች
18 ጁኡዲቲዝ ኦሲንቦ – 16 ቶስካህ ሀሳቪይቪንዳ – 20 ዲያና ዋቼራ – 5 ሌሀ ቼሮቲች – 19 ራቻኤሊ ኦቶሮ – 9 ስቴላ አታንጎ – 6 ቬሮኒካ አሩም

ሰላም የተከበራችሁ የሶከር ኢትዮጵያ ተከታታዮች በሀዋሳ አለም አቀፍ ስታድየም በኢትዮጵያ እና ኬንያ መካከል የሚደረገውን የአለም ከ20 አመት በታች ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል፡፡

መልካም ቆይታ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *