​የወልዲያ ተጫዋቾች ቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ሊያቋርጡ ነው

የወልዲያ ተጨዋቾች እና የቡዱኑ አባላት ከስምምነት የደረሱት ክፍያ ባለመፈፀሙ ምክንያት ዝግጅት አቋርጠው ወደ ወልዲያ ሊመለሱ ነው ።

ከነሐሴ 21 ጀምሮ በሀዋሳ ከተማ ገዛኸኝ አበራ ሪዞርት ሙሉ ቡድኑ ዝግጅቱን እንደጀመረ ይታወቃል። ሆኖም በበአል ምክንያት ለእረፍት ቡድኑ ከተበተነ በኋላ ወደ ዝግጅት ሲመለሱ ከቡድኑ አባላት መካከል ዘንድሮ የተቀላቀሉት ቢያድግልኝ ኤልያስ ፣ ምንያህል ተሾመ እና ፍፁም ገ/ማርያም ያለፉትን ስምንት ቀናት ልምምድ ያቋረጡ ሲሆን የተቀሩት የቡድኑ አባላት በስምምነት ደረጃ የተስማሙት ክፍያ ባለመፈፀሙ ምክንያት ቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን  አቋርጠው ሊወጡ እንደሚችሉ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ማረጋገጫ አግኝተናል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የሚመለከታቸው የክለቡ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ገረመውን ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረግነው ጥረት ያልተሳካ ቢሆንም የክለቡ የበላይ ኃላፊዎች በዚህ ጉዳይ ላይ የሚጡት ምላሽ ካለ የምናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።

ወልድያ መስከረም 13 በሚጀመረው የደቡብ ካስትል ዋንጫ ላይ እንደሚሳተፍ የተረጋገጠ ቢሆንም የቡድኑ አባላት ዝግጅታቸውን አቋርጠው የሚሄዱ ከሆነ ተሳታፊ የመሆናቸው ጉዳይ አጠራጣሪ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *