​መቐለ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል

በዝውውር መስኮቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሳተፈ የሚገኘው መቐለ ከተማ መድሀኔ ታደሰ እና ዮናስ ግርማይን አስፈርሟል፡፡

መድሀኔ ታደሰ ትራንስን ከለቀቀ ከ10 አመታት በኋላ በድጋሚ ወደ መቐለ የተመለሰበትን ዝውውር በማድረግ ለመቐለ ከተማ የ1 አመት ውል ፈርሟል፡፡ በትራንስ ኢትዮጵያ የተሳኩ አመታትን አሳልፎ በ1999 ወደ መከላከያ ያመራው መድሀኔ በ1997 የፕሪምየር ሊጉ ከፍተኛ ግብ አግቢ ከመሆኑ በተጨማሪ በ2003 ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የሊጉን ዋንጫ አንስቷል፡፡ በዳሽን ቢራ ፣ መከላከያ (በድጋሚ) እና ሀዋሳ ከተማም ተጫውቶ አሳልፏል፡፡

ሌላው ለክለቡ የፈረመው ተጫዋች ዮናስ ግርማይ ነው፡፡ የመሀል ተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ በትራንስ ኢትዮጵያ ፣ ዳሽን ቢራ ፣ ሰበታ ከተማ እና ዳሽን ቢራ የእግርኳስ ህይወቱን አሳልፏል፡፡

መቐለ ከተማ እስካሁን 4 የውጪ ዜጋ ተጫዋቾችን ጨምሮ በአጠቃላይ 13 አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *