​ፌዴሬሽኑ በብሩክ ቃልቦሬ ጉዳይ ላይ ውሳኔ አሳልፏል

ብሩክ ቀልቦሬ በአዳማ ከተማ የነበረውን የውል ዘመን አጠናቆ ለድሬዳዋ ከተማ ፊርማውን ያኖረ ቢሆንም በኋላ ላይ ለወልድያ ዳግመኛ በመፈረሙ ለሁለት ክለብ ፊርማ በማኖሩ ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሲታይ ቆይቷል፡፡

ብሩክ ለሁለት ክለብ መፈረሙ ስህተት እንደሆነ አምኖ በይፋ ይቅርታ በመጠየቁ እንዲሁም ለኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የይቅርታ ደብዳቤ በማስገባሁ እና የድሬዳዋ ከተማ በብሩክ ቀልቦሬ ላይ አብሮት ለመቀጠል ፍላጎት ባለማሳየቱ ወደ ወልዲያ አምርቶ እንዲጫወት ውሳኔ አሳልፏል።

ብሩክ ቀልቦሬ በአሁን ሰአት ቦትስዋና ከሚያቀናው የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በፊርማ ክፍያ ምክንያት ከወልዲያ ጋር ስምምነት ካላደረጉት አራት ተጨዋቾች መካከል አንዱ በመሆን እስካሁን ከወልድያ ጋር ዝግጅት እንዳልጀመረ ተሰምቷል።

በተያያዘ ዜና በአክሊሉ አያነው የይገባኛል ጥያቄ ፋሲል ከነማ እና በኢትዮዽያ ቡና መካከል ውዝግብ የተፈጠረ መሆኑን ተከትሎ የኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉዳዩን ተመልክቶ ውሳኔ እንዲሰጥበት ለዲሲፒሊን ኮሚቴ የመራው መሆኑ ሲታወቅ አክሊሉ ከኢትዮዽያ ቡና ጋር ዝግጅት እያደረገ ከመሆኑ ባሻገር በደቡብ ካስቴል ዋንጫ ላይ የኢትዮዽያ ቡናን ማልያ ለብሶ እየተጫወተ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *