የየክለቦቹ የዝውውር ወሬዎች

የክረምቱ የዝውውር እንቅስቃሴ ከሃምሌ አንድ ወዲህ ተጧጡፎ ቀጥሏል፡፡ ሶከር ኢትዮጰያም ከተለያዩ ምንጮች የሰበሰበቻቸውን የተረጋገጡ እና በሂደት ላይ የሚገኙ ዝውውሮችን እንዲሁም የኮንትራት ማራዘምያ ስምምነቶችን እንዲህ አጠናቅራለች፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ

-እስካሁን ፋሲካ አስፋው እና መሃሪ መናን ያስፈረሙ ሲሆን በርካታ ተጫዋቾች ከክለቡ በመልቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

-ሮበርት ኦዶንግካራ እና አይዛክ ኢሴንዴ ከክለቡ መለያየታቸው እርግጥ ሆኗል፡፡ ሁለቱ ተጫዋቾች ከቢድቬትስ ዊትስ እና ጆሞ ኮስሞስ ክለቦች ጋር መነጋገራቸው ተወርቷል፡፡

-ቢያድግልኝ ኤልያስ ለሙከራ ወደ ደቡብ አፍሪካ አቅንቷል፡፡ ሁለገቡ ተከላካይ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚያደርገው ጉዞ ካልተሳካ ደደቢትን ሊቀላቀል ይችላል፡፡

-ዊልያም ኤሳድጆ ፣ ያሬድ ዝናቡ ፣ አበባው ቡታቆ ፣ ዮናታን ብርሃኔ ፣ ዘካርያስ ቱጂ ፣ ዘሪሁን ታደለ እና ምንተስኖት አዳነም አዲስ ኮንትራት ያልቀረበላቸው ሲሆን ከክለቡ የመልቀቅ እድላቸውም ሰፊ ነው ተብሏል፡፡

-ሳሚ ሳኑሚ ወደ ደደቢት ሮበርት ኦዶንግካራ እና አይዛክ ኢሴንዴ ደግሞ ወደ ደቡብ አፍሪካ ያቀኑበት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከዩጋንዳ እና ማሊ ለ5 ተጫዋቾች የሙከራ እድል የሰጠ ሲሆን በቅርቡ በተጫዋቾቹ ላይ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

– ከአሌሳንድሪያ ካለ ስምምነት የተመለሰው ሽመልስ በቀለ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊመለስ ይችላል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና

-አደገኞቹ የቀድሞ ተጫዋቻቸው ወሰኑ ማዜን መልሰው ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምረዋል፡፡ ተጫዋቹ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቀረበለትን የውል ማራዘም ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

-ለደደቢት ለመፈረም ተቃርቦ የነበረው የአዳማ ከነማው አጥቂ በረከት አዲሱ ከኢትዮጰያ ቡና ጋር በድርድር ላይ ይገኛል፡፡ አንጋፋው አጥቂ ከሁለቱ ክለቦች ለአንዱ በእርግጠኝነት እንደሚፈርም ተማምኗል፡፡

-ቡና የመከላከያውን ባለተሰጥኦ ተክለወልድ ፍቃዱ ፣ በኃይሉ ግርማ እና ምንተስኖት አዳነን ለማዘዋወር በጥረት ላይ ነው፡፡

-8 ተጫዋቾች ከጋና ፣ ቤኒን እና ናይጄርያ ለሙከራ ኢትዮጵያ ቡና ይመጣሉ፡፡

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

-እስካሁን 8 ተጫዋቾችን ያስፈረመው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወሳኝ አጥቂውን ፊሊፕ ዳውዚን ኮንትራት አራዝሟል፡፡ ባንክ ለናይጄርያዊው ኮንትራት ማራዘምያ ከ700ሺህ ብር በላይ ወጪ አድርጓል፡፡

-አብይ በየነ እና ወሰኑ ማዜ ከክለቡ ጋር የማይቀጥሉ ሲሆን የኤልያስ ማሞ ኮንትራት በመጠናቀቁም የመልቀቁ እድል ሰፊ ነው፡፡


መከላከያ

-ጦሩ የኮከቡ ፍሬው ሰለሞንን ኮንትራት አራዝሟል፡፡ የአጥቂ አማካዩ ስሙ ከበርካታ ክለቦች ጋር ሲያያዝ መሰንበቱ ይታወቃል፡፡

-መከላከያ ከበርካታ ክለቦች ቀድሞ የበረከት ይስሃቅን ፊርማ ሊያገኝ ጫፍ ደርሷል፡፡

-መስኡድ መሃመድ እስካሁን ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ያለውን ውል አለማራዘሙን ተከትሎ መከላከያአማካዩን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይቷል፡፡

-መሃመድ ናስር ወደ ዱባይ የሚያደርገው ጉዞ ካልቀናው የቀድሞ ክለቡን ሊቀላቀል ይችላል፡፡

ዳሽን ቢራ

-ዳሽን ቢራ በዚህ ክረምትም ከፍተኛውን ገንዘብ ያፈሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የጎንደሩ ክለብ ለቅዱስ ጊዮርጊሱ የግራ መስመር ተከላካይ ዝውውውር ከ1 ሚልዮን ብር በላይ ለማውጣት መዘጋጀቱ ተነግሯል፡፡ አበባው ከጊዮርጊስ መልቀቁ እንደማይቀር የተነገረ ሲሆን የውጭ ሃገራት የዝውውር እድሎች ካልተሳኩ ለዳሽን ይፈርማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

– በበርካታ ክለቦች የሚፈለገው የሙገሩ ተከላካይ ቴዎድሮስ መሳይ በዳሽን ቢራም ይፈለጋል፡፡


ሙገር ሲሚንቶ

-ሙገር ዘንድሮም እንደቀደሙት ጊዜያት ወሳኝ ተጫዋቾችን ለማቆየት ተቸግሯል፡፡ በቡድኑ ወሳኝ ተጫዋቾች የሆኑት ግብ ጠባቂው አሰግድ አክሊሉ ፣ ሙጂብ ሳኒ ፣ በሃይሉ ግርማ እና ቴዎድሮስ መሳይ የመቆየታቸው ጉዳይ አጠራጣሪ ነው፡፡

-ሙገር ወሳኝ አጥቂው አኪም አካንዴ ወደ ንግድ ባንክ ሲያመራበት የሌላኛውን አጥቂ ጌድዮን አካፓ ኮንትራት አራዝሟል፡፡ ሙገር ከማራዘምያው 350ሺህ ብር መክፈሉ ተነግሯል፡፡

-ሙገር ከጌድዮን በተጨማሪ የእንግዳወርቅ አሰፋ ፣ እስክንድር አብዱልሃሚድ ፣ ሄኖክ ፍስሃ እና አለማየሁ አየለን ኮንትራት አራዝሟል፡፡


ወላይታ ድቻ

ወላይታ ድቻ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ባመራበት ወቅት የአመዛኞቹ ተጫዋቾች ኮንትራት በመራዘሙ አመዛኞቹ ተጫዋቾች የ1 አመት ቀሪ ኮንትራት ይቀራቸዋል፡፡

-ወሳኙ የቡድኑ አማካይ አሸናፊ ሽብሩ ስሙ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዝውውር ጋር ተያይዟል፡፡


አርባምንጭ ከነማ

አርባምንጭ ከነማ ዘንድሮም እንዳምናው በተጫዋቾች ዝውውር ላይ የመሳተፍ ፍላጎት አላሳየም ፡፡ እስካሁንም በይፋ የፈረመ እና በጭምጭምታ ደረጃ የሚወራ ዝውውር የለም፡፡ ከክለቡ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱትም ክለቡ እስካሁን የዝውውር እንቅስቃሴ አልጀመረም፡፡


መብራት ኃይል

-አብዱልከሪም ሃሰንን ለንግድ ባንክ አሳልፎ የሰጠው መብራት ኃይል የበረከት ይስሃቅን ኮንትራት አላራዘመም፡፡

-አሰልጣኝ ዮርዳን ስቶይኮቭ ከባህርዳር ተመልሰዋል፡፡ ቡልጋርያዊው ከባህርዳሩ ውድድር ተጫዋቾች ያግኙ አያግኙ የታወቀ ነገር የለም፡፡

-ቀዮቹ የቅዱስ ጊዮርጊሱን ወጣት ዘካርያስ ቱጂን ፊርማ ለማግኘት ጫፍ ደርሰዋል፡፡ ዘካርያስ በግራ መስመር ተከላካይ እና አማካይ ሆኖ መጫወት ይችላል፡፡


ደደቢት

-ሰማያዊው ጦር ከአምናው ስህተቱ የተማረ ይመስላል፡፡ ደደቢት የበርካታ ወሳኝ ተጫዋቾቹን ኮንትራት ያራዘመ ሲሆን አዳዲስ ግዢዎችንም እየፈፀመ ነው፡፡ በተለይም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ያስፈረማቸው በሂደት ላይ የሚገኙ ዝውውሮች ትኩረትን ስቧል፡፡

-የሳሙኤል ሳኑሚ መፈረም ሲረጋገጥ የያሬድ ዝናቡ መቀላቀልም ከጫፍ ደርሷል፡፡ ሁለገቡ የቀድሞ የአዳማ ከነማ አምበል የቀረው ከደደቢት ኃላፊዎች ጋር በአከፋፈል ሁኔታ ላይ መስማማት ነው፡፡

-ደደቢት የሙገር ሲሚንቶው አምበል በሃይሉ ግርማን ለማስፈረም የሚደረገውን ሩጫ ተቀላቅሏል፡፡ የቅጣት ምት ስፔሻሊስቱ ከደደቢት በተጨማሪ በመከላከያ ፣ ንግድ ባንክ እና ኢትዮጵያ ቡና ይፈለጋል፡፡

-ደደቢት በቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋቾች ላይ ማማተሩን ቀጥሏል፡፡ ዊልያም ኤሳድጆ ፣ ምንተስኖት አዳነ እና ዮናታን ብርሃኔን ለማስፈረም እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡


ሀዋሳ ከነማ

-ከዋና አሰልጣኙ ታረቀኝ አሰፋ ጋር የተለያየው ሀዋሳ ከነማ ምክትሉ በፍቃዱ ዘሪሁን በድጋሚ ክለቡን ሊረከብ ይችላል፡፡

-ሀዋሳ በሙገሩ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ቴዎድሮስ መሳይ ላይ ትኩረቱን አሳርፏል፡፡

n ምንጮች – ፕላኔት ስፖርት (ሬድዮ) እና ዛሚ ስፖርት ብሄራዊ (ሬድዮ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *