አጫጭር ዜናዎች

—- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በወርሃዊው የፊፋ ደረጃ ካለፈው ወር 3 ደረጃዎችን ወርዶ 110ኛ ላይ ተቀምጧል፡፡ የአለም ሻምፒዮኗ ጀርመን የ1ኝነት ደረጃውን ከስፔን ተረክባለች፡፡

— ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ስፔን በነሀሴ ወር አጋማሽ ለወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያመራ ታውቋል፡፡ፈረሰኞቹ የባርሴሎና ጉዞ ወጪ ሙሉ ለሙሉ በኤ.. ራማሳ ክለብ የሚሸፈን ይሆናል፡፡ በቆይታቸውም ከወዳጅነት ጨዋታ ባለፈ በባርሴሎና ከተማ የተለያዩ ሙዚየሞችን ኑካምፕን ጨምሮ የሚጎበኙ ይሆናል፡፡

—የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ ኮከብ ጋናዊው አብርሃም ኩዲሞር የቤልጅየሙን ክለብ ቻርሌሮይ ወደ ሳኡዲ አረብያው አል ፈታህ ክለብ ተዘዋውሯል፡፡ አብርሃም ከ1996 እስከ 1999 በቅዱስ ጊዮርጊስ ቆይቷል፡፡

—የካፍ የአሰልጣኞች ስልጠና ለB እና C ፍቃድ ላላቸው አሰልጣኞች እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡ 23 ሴት ዳኞችም የብቃት ማሻሻያ ስልጠና ይሰጣል፡፡ 18 ፌድራል ዳኛ ሲሆኑ የተቀሩት 5 ደግሞ ኢንተርናሽናል ሴት ዳኞች ናቸው፡፡

—ቅዱስ ጊዮርጊስን ለቆ ወደ ግብፁ ኢትሀድ አሌሳንድሪያ ያመራው ኡመድ ኡክሪ ወደ ግብፅ አምርቶ የአሌሳንድሪያውን ክለብ ለቅድመ ውድድር ዝግጅት የሚቀላቀል ይሆናል፡፡ ኡመድ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ከአልጄሪያው ጨዋታ 1 ሳምንት ቀደም ብሎ ይቀላቀላል፡፡ (ፕ.ስ)

—የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወደ ሀዋሳ በመጓዝ ልምምድ ጀምሯል፡፡ የዋልያዎቹ አሰልጣኝ 32 ተጫዋቾችን በመያዝ ነው ልምምድ የጀመሩት፡፡ በሀዋሳም 1 ወር የሚቀዩ ይሆናል፡፡

—የኢትዮጵያ 17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በመጪው እሁድ ከጋቦን አቻው ጋር ኒጀር ላይ ለሚካሄደው የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች ውድድር ለማለፍ የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡ በዮሀንስ ሳህሌ የሚመሩት ቀይ-ቀበሮዎቹ 1 ወር በላይ ሀዋሳ ለዝግጅት ቆይተዋል፡፡

—የካፍ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ በመስከረም ወር አዲስ አበባ ላይ አንደሚደረግ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን አስታውቋል፡፡ ስብሰባው 10 ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡

—አዲሱ የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ጥላሁን መንገሻ በባህርዳር በመካሄድ ላይ በሚገኝው የብሄራዊ ሊግ ውድድር ላይ ተጫዋቾችን መመልመል ሳይችሉ እንደተመለሱ ተነግሯል፡፡ ጥላሁን የተመለከቱት ቡና ለተለያዩ ክለቦች በውሰት የሰጣቸውን ተጫዋቾች ብቻ ነው፡፡ (ፕ.ስ)

—የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን በዓመቱ መጨረሻ ለኮኮቦች የሚሰጠው የገንዘብ ሽልማት እስካሁን እንዳልሰጠ ተነግሯል፡፡ (ፕ.ስ)

—የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ሩዋንዳ ላይ ለሚካሄደው የሴካፋ ክለቦች ውድድር ላይ እንዲሳተፍ ግብዣ እንደቀረበለት ታውቋል፡፡ ቡና በሴካፋ ፓል ካጋሜ ካፕ ይሳተፍ አይሳተፍ ከክለቡ የተሰጠ ማረጋገጫ እስካሁን የለም፡፡ (ፕ.ስ)

—የሀረር ሲቲ አብዛኞቹ ተጫዋቾች ውላቸውን በመጨረሳቸው ክለቡን ለመልቀቅ ከጫፍ መድረሳቸው ተወርቷል፡፡ ክለቡ ባሳለፍነው ውድድር ወደ ከፍተኛ ብሄራዊ ሊግ መውረዱ የሚታወስ ነው፡ (ፕ.ስ)

—የሱዳኑ ሃያል ክለብ አል-ሂላል በኢትዮጵያ ለ10 ቀናት ቆይታ በማድረግ ዝግጅት እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ የኦምዱርማኑ ክለብ በቆይታው ከደደቢት እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ግንኙነት መጀመሩ ታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *