የሽመልስ በቀለ ሁለት ግቦች ፔትሮጀት ስሞሃ ላይ ድል እንዲቀዳጅ አስችለዋል

በግብፅፅ ፕሪምየር ሊግ 22ኛ ሳምንት በአል ስዌዝ ስታዲየም የሁለቱ ኢትዮጵያዊያንን ክለቦች ያገናኘው ጨዋታ በፔትሮጀት 2-1 አሸናፊነት ተደምድሟል፡፡ ፔትሮጀት በሽመልስ በቀለ ሁለት ግቦች ታግዞ ሰማያዊ ሞገዶቹን ሲረታ ኡመድ ኡኩሪ በተቃራኒ ሆኖ የቀድሞ የክለብ አጋሩን ገጥሟል፡፡

ሽመልስ ለአራተኛ ተከታታይ ጨዋታ ፔትሮጀትን በአምበልነት በመራበት ግጥሚያ እንግዶቹ በመጀመሪያው ክፍለ ግዜ ከባለሜዳዎቹ ተሽለው ታይተዋል፡፡ ሆኖም ሁለቱም ክለቦች የሚቀስ የግብ ሙከራ ማድረግ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ ኡመድ በመጀመሪያው አጋማሽ ከግራ መስመር የተሻገረለትን ኳስ ጨርፎ ወደ ውጪ የወጣበት ሲሆን ስሞሃ ከነበረው የጨዋታ የበላይነት አንፃር የጠሩ የግብ እድሎችን መፍጠር አለመቻሉ እንዲሁም የፔትሮጀት የተቆራረጠ የቅብብሎሽ ስኬት የመጀመሪያው 45 መለያ ነበሩ፡፡ ኡመድ በ43ኛው ደቂቃ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመዞበታል፡፡

በሁለተኛው አጋማሽ የመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ባለሜዳዎቹ በተሻለ ከሽመልስ በሚነሱ ኳሶችን እድሎችን ለመፍጠር ሲጥሩ ታይተዋል፡፡ በተለይ በ50ኛው ደቂቃ ከሽመልስ የተነሳው ኳስ አጥቂው ቤንጃሚን ቢያገኝም የስሞሃ ተከላካዮች ኳስ አውጥተውበታል፡፡ ሆኖም ቤንጃሚን ላይ ጥፋት ተሰርቷል በሚል የፍፁም ቅጣት ይገባናል ቢሉም የመሃል አርቢትሩ መሃመድ አቡ ካተር ሳይቀበሉ ቀርተዋል፡፡ ስሞሃ በግዜ ሂደት ዳግም ጨዋታውን መመለስ ቢችልም በ70ኛው ደቂቃ ሽመልስ ባስቆጠረው ግብ መሪ መሆን ችለዋል፡፡ ከሁለት ደቂቃዎች በኃላ ኢትዮጵያዊው ጥበበኛ የግል ብቃቱን ተጠቅሞ መሪነቱን ወደ ሁለት ከፍ አድርጓል፡፡ ሽመልስ የስሞሃን አማካይ ከነጠቀ በኃላ በግብ ጠባቂው እግሮች መሃከል በማሾለክ አስቆጥሯል፡፡ ግቡን ካስቆጠረ በኃላ ሽመልስ ደስታው የገለፀው የማዕዘን መምቻ ባንዲራውን በመምታት ሲሆን በአስገራሚ ሁኔታ የመሃል አርቢትሩ የቢጫ ካርድ አሳይተውታል፡፡ በ74ኛው ደቂቃ ኡመድ በጋናዊው የቀድሞ የአል ሂላል እና ኤል ሜሪክ ኮከብ ኦውገስቲን ኦክራ ተቀይሮ ከሜዳ ወጥቷል፡፡

ስሞሃዎች በ78ኛው ደቂቃ ታሪቅ ጠሃ አብዱልሃሚድ በግሩም ሁኔታ ባስቆጠረውን ቅጣት ምት ነጥብ ለመጋራት ቢቃረቡም ፔትሮጀቶች መሪነታቸውን አስጠብቀው ጨዋታውን ማሸነፍ ችለዋል፡፡ ሽመልስ በ79ኛው ደቂቃ ላይ በመሃመድ ሙስጠፋ ተቀይሮ ከሜዳ ወጥቷል፡፡

ሉጉን አሁንም የአምናው ቻምፒዮን አል አሃሊ በ51 ነጥብ ሲመራ ፔትሮጀት በ28 ነጥብ ደረጃውን ወደ 9ኛ ከፍ ሲያደርግ ስሞሃ ሁለት ደረጃ ካለው ኤስማኤሊ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት የሚያጠብበትን እድል አበላሽቷል፡፡ ስሞሃ በ35 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡


የሽመልስ በቀለን ጎሎች ሊንኩን በመጫን ይመልከቱ | LINK

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *