መቐለ ከተማ አምስት ተጫዋቾችን ቀንሷል

በዘንድሮ የውድደር አመት ከከፍተኛ ሊግ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ያደገው እና በሊጉ ላይ በግሩም ሁኔታ ግስጋሴ እያደረገ የሚገኘው መቐለ ከተማ አምስት ተጫዋቾች ከክለቡ መቀነሱን አስታወቀ።

ክለቡ ከአንድ ወር በፊት የመጨረሻ ማስጠንቀቅያ ከሰጣቸው ተጫዋቾች መካከል ዱላ ሙላቱ፣ ዮሴፍ ድንገቱ፣ ዮሴፍ ኃይሉ፣ ሙሉጌታ ረጋሳ እና ተመስገን አዳሙ ከክለቡ የተቀነሱት ተጫዋቾች መሆናቸው ታውቋል።

ከክለቡ ከተቀነሱት ተጨዋቾች መካከል ዱላ ሙላቱ፣ ዮሴፍ ድንገቱ እና ሙሉጌታ ረጋሳ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ቡድኑን መቀላቀላቸው የሚታወስ ሲሆን በሚጠበቀው መልኩ ቡድኑን እያገለገሉ ባለመሆናቸው የተቀሱ ሲሆን ሌሎቹ ሁለት ተጫዋቾች ባለፈው አመትም የነበሩ ተጫዋቾች ናቸው።

የአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ስብስብ የጥር የዝውውር መስኮት ከመከፈቱ በፊት በዝውውሩ በስፋት እየተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን ሁለት የውጪ ዜግነት ያላቸውን ተጨዋቾች እና ቶክ ጀምስን ከማስፈረሙ በተጨማሪ ለካርሎስ ዳምጠው እና ለእያሱ በቀለ የሙከራ እድል ሰጥቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *