​ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ | ወላይታ ድቻ በዛንዚባር የመጀመርያ ልምምዱን አከናውኗል

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ ከዛንዚባሩ ዚማሞቶ ጋር ላለበት የመጀመርያ ጨዋታ ትላንት ወደ ስፍራው ያቀናው ወላይታ ድቻ  የመጀመርያ ልምምዱን አደርጓል።

በአሰልጠኝ ዘነበ ፍስሀ እየተመራ በጥሩ መነቃቃት ላይ የሚገኘው ቡድኑ በትላንትናው እለት ረፋድ 04:00 ላይ 19 ተጨዋቾችን ጨምሮ በአጠቃላይ 31 የልኡካን ቡድን በመያዝ ዛንዚባር የደረሰ ሲሆን በውሃ በተከበበው አብላ ቢች ሆቴል ማረፊያውን አድርጎ ይገኛል።

ቡድኑ ዛንዚባር ከገባ የመጀመርያ ልምምዱን ዛሬ 10:00 ላይ በሚጫወትበት የሰው ሰራሽ ሜዳ  (አማን ስቴዲየም) 1:50 ሰዓት የፈጀ ልምምድ አከናውኗል። ለሁለት ተከፍሎ መጫወት እና የማሟሟቅ ስራዎች የልምምዱ አካል የነበሩ ሲሆን ሁሉም ተጫዋቾች በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ እና ለእሁድ ጨዋታ ጥሩ ፍላጎት እና ተነሳሽነት እንዳለ ከስፍራው ሰምተናል።

በሞቃታማ የአየር ሁኔታ ላይ የምትገኘው ከተማዋ እሁድ 10:00 ላይ የዚማሞቶ እና የወላይታ ድቻን ጨዋታ ታስተናግዳለች። 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *