ቻምፒየንስ ሊግ | የቅዱስ ጊዮርጊስ እና አል ሰላም ዋኡ ጨዋታ መካሄድ አጠራጥሯል

በካፍ ቶታል ቻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ አዲስ አበባ ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአል ሰላም ዋኡ ጋር የሚደርገው ጨዋታ መካሄዱ አሁንም አጠራጣሪ ሆኗል፡፡ አል ሰላም ዋኡ ቅዳሜ ጠዋት ወደ አዲስ አበባ ይመጣል የሚሉ መረጃዎች በስፋት ተገግሮ የነበረ ቢሆንም ክለቡ ግን እስከምሽት የመምጣጡ ነገር አጠራጣሪ መሆኑን ለፌድሬሽኑ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሶከር ኢትዮጵያ ጠቁመዋል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን ለካፍ ጨዋታውን በተመለከተ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ለማሳወቅ ጥረት ጀምረዋል፡፡ አል ሰላም ዋኡ ጨዋታው እንዲራዘምለት ለካፍ ጥያቄ ማቅረቡ አይቀሬ እንደሆነ ከደቡብ ሱዳን የሚወጡ መረጃዎች ቢጠቁሙም የአፍሪካ እግርኳስን በበላይነት የሚመራው አካል ግን ውሳኔውም የሚቀበል አይመስልም፡፡ ካፍ በክለቦች የዝግጁነት ችግር ምክንያት ጨዋታዎችን ሲያራዝም እምብዛም አንመለከትም፡፡ ይህንን ተከትሎም አል ሰላም ዋኡ ከቻምፒየንስ ሊጉ ላለመውጣት የግድ የካፍን አዎንታዊ ውሳኔን መጠበቅ የግድ ይለዋል፡፡

የደቡብ ሱዳኑ አል ሂላል ጁባ ከቱኒዚያው ዩኒየን ስፖርቲቭ ደ ቤን ጎርዳን ጋር ለሚያደርገው የካፍ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ሰዓታት ሲቀሩት ወደ ስፍራው ዛሬ ጠዋት መድረሱን ተከትሎ ጨዋታው እንዲራዘምለት ለካፍ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡ ደቡብ ሱዳን ላይ ባለው የፓለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት በአፍሪካ የክለብ ውድድሮች የሚሳተፉ የሃገሪቱ ክለቦች ከዝግጅት እና ፋይናን እጦት እየተፈተኑ ይገኛሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *