የ2018 ካፍ ቻምፒየንስ ሊግ በሳምንቱ መጨረሻ ተጀምሯል

በካፍ ቶታል ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ቅዳሜ እና እሁድ በተደረጉ ጨዋታዎች ተጀምረዋል፡፡ በተደረጉ ጨዋታዎች በርካታ ግቦች የተቆጠሩ ሲሆን አንድ ጨዋታ ብቻ ግብ ሳይሰተናገድ ተጠናቋል፡፡ የሞሮኮው ዲፋ ኤል ጃዲዳ 10 ግቦችን ያስቆጠረበት ጨዋታ በቻምፒየንስ ሊጉ ታሪክ በሰፊ የግብ ልዩነት የተጠናቀቀ ጨዋታ ሆኖ አልፏል፡፡

የኬንያው ቻምፒዮን ጎር ማሂያ ማቻኮስ ላይ የኤኳቶሪያል ጊኒውን ሊዮኔስ ቬጅታሪያኖስን አስተናግዶ 2-0 አሸንፏል፡፡ ኬቨን ኦሞንዲ እና ጉኪያን ኤፍሬም የጎርን የማሸነፊያ ግቦች ከመረብ አዋህደዋል፡፡ የሱዳኑ ኤል ሜሪክ በፋይናንስ ቀውስ እና የተጫዋቾች ጉዳት ተዘፍቆ ቦትስዋና ላይ ያደረገውን ጨዋታ በታውንሺፕ ሮለርስ 3-0 ተሸንፏል፡፡ የሜሪክ የከተማ ተቀናቃኙ አል ሂላልም ወደ ላይቤሪያ አምርቶ በሊስክር 1-0 ተሸንፏል፡፡ የዩጋንዳው ኬሲሲኤ በስናፕስ ስፖርትስ 2-1 የተሸነፈ ሲሆን የአልጄሪያው ኢኤስ ሴቲፍ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ክለብ የሆነውን ኦሎምፒክ ሪያል ባንጉዊን 6-0 እንዲሁም የሞሮኮውን ጃዲዳ የጊኒ ቢሳውን ቤኔፊካ ቢሳውን 10-0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፈዋል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ የደቡብ ሱዳኑን አል ሳልም ዋኡ እሁድ አዲስ አበባ ላይ ያስተናግድ የነበረ ቢሆንም ዋኡ ለጨዋታው በሰዓቱ መድረስ ባለመቻሉ ፈረሰኞቹ በቀጥታ ወደ ተከታዩ የማጣሪያ ዙር ማለፍ ችለዋል፡፡

የተመዘገቡት ውጤቶችን እነዚህን ይመስላሉ

ጎር ማሂያ (ኬንያ) 2-0 ሊዮኔስ ቬጅታሪያኖስ (ኤኳቶሪያል ጊኒ)

ስናፕስ ስፖርትስ (ማዳጋስካር) 2-1 ኬሲሲኤ (ዩጋንዳ)

ያንግ አፍሪካንስ (ታንዛኒያ) 1-0 ሴንት ሉዊ ሰንስ (ሲሸልስ)

ዛናኮ (ዛምቢያ) 3-0 ጋምቢያ አርምድ ፎርስ (ጋምቢያ)

ጄኬዩ (ዛንዚባር) 0-0 ዜስኮ ዩናይትድ (ዛምቢያ)

ራዮን ስፖርትስ (ሩዋንዳ) 1-1 ኤልኤልቢ አካዳሚክ (ቡሩንዲ)

ታውንሺፕ ሮለርስ (ቦትስዋና) 3-0 ኤል ሜሪክ (ሱዳን)

ስታ ማሊያን (ማሊ) 1-1 ዊልያምስቪል (ኮትዲቯር)

ሪያል ክለብ ካዲዮጎ (ቡርኪና ፋሶ) 1-0 ሲኤፍ ሞናና (ጋቦን)

ኤኤስ ፋን (ኒጀር) 1-3 ሆሮያ (ጊኒ)

ቤድቬስት ዊትስ (ደቡብ አፍሪካ) 2-0 ፓምፕለሞስስ (ሞሪሺየስ)

አሳክ ኮንኮርድ (ሞሪታንያ) 1-1 ኤስራንስ ደ ቱኒዝ (ቱኒዚያ)

ጄኔሬሽን ፉት (ሴኔጋል) 2-0 ምስር ኤል ማቃሳ (ግብፅ)

ኤሲ ሊዮፓርድስ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) 2-1 ኤኤስ ቶጎ ፖርት (ቶጎ)

ዲፋ ኤል ጃዲዳ (ሞሮኮ) 10-0 ቤንፊካ ቢሳው (ጊኒ ቢሳው)

ንጋያ ክለብ (ኮሞሮስ) 1-1 ዩዲ ሶንጎ (ሞዛምቢክ)

ፕሌቶ ዩናይትድ (ናይጄሪያ) 3-0 ኢዲንግ ስፖርት (ካሜሮን)

ባፍልስ ዱ ቦርጎ (ቤኒን) 1-1 አሴክ ሚሞሳስ (ኮትዲቯር)

ኤኤስ ሪያል ባማኮ (ማሊ) 1-1 ማውንቴን ኦፍ ፋየር ሚኒስትሪ (ናይጄሪያ)

ኤኤስ ቪታ ክለብ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) 4-0 ማይቲ ዋንደረርስ (ማላዊ)

ፕሪሜሮ ደ አጎስቶ (አንጎላ) 3-0 ፕላቲኒየም (ዚምባቡዌ)

ኢኤስ ሴቲፍ (አልጄሪያ) 6-0 ኦሎምፒክ ሪያል ባንጉዊ (ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ)

ሊስክር (ላይቤሪያ) 1-0 አል ሂላል (ሱዳን)

ኤኤስ ኦቶ ዶዮ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) 2-0 ኤምሲ አልጀር (አልጄሪያ)

ባንቱ ኤፍሲ (ሌሶቶ) 2-4 ምባባኔ ስዋሎስ (ስዋዚላንድ)

አል ታሃዲ (ሊቢያ) 1-0 አዱና ስታርስ (ጋና)

ቅዱስ ጊዮርጊስ በፎርፌ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *