የኮንፌድሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ተጀምረዋል

የቶታል ካፍ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ በተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች በሳምነቱ መጨረሻ በተደረጉ ጨዋታዎች ተጀምረዋል፡፡ ድራማዊ ክስተት የያዩበት የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ ለመጀመሪያ ግዜ በውድድሩ ላይ እየተካፈለ የሚገኘው ወላይታ ድቻ ከሜዳው ውጪ ከዛንዚባሩ ዚማሞቶ ጋር አቻ ተለያይቷል፡፡

የሩዋንዳው ኤፒአር የሲሸልሱን አንስ ሪዩኒየን ኪጋሊ ላይ ገጥሞ 4-0 አሸንፏል፡፡ ጂሃድ ቢዚማና ሃትሪክ ሲሰራ ኢሳ ቢጊሪማና አንድ ግብ ለኤፒአር አክሏል፡፡ የጋናው አሻንቲ ኮቶኮ እና የኮንጎው ካራ ብራዛቪል ያደረጉት ጨዋታ ብዙዎችን ያስገረመ ክስተት አስተናግዷል፡፡ ከጨዋታው አንድ ቀን አስቀድሞ የካራ ብራዛቪል ተጫዋቾች በባባ ያራ ስፖርትስ ስታዲየም የመጨረሻ ልምምድ ከማድረግ ይልቅ በግቦቹ አቅራቢ የውሃ ሽንት መሽናታቸው የኮቶኮ ሃላፊዎች ያስቆጣ ሲሆን በጨዋታው ላይ አምስት የፍፁም ቅጣት ምቶች ተሰጥተው ኮቶኮ 1-0 አሸንፏል፡፡ ከተሰጡት አምስት ፍፁም ቅጣት ምቶች ኮቶኮ አራት አግኝቶ ሶስቱን ሲያመክን ካራ ብራዛቪል በአንፃሩ አንድ ስቷል፡፡ የኮቶኮን ማሸነፊያ ግብ ያኩቡ መሃመድ በፍፁም ቅጣት ምት አስገኝቷል፡፡

ከቻን ዋንጫ አሸናፊነት በኃላ ወደ ጨዋታ የተመለሰው ሞሮኳዊው አጥቂ አዩብ ኤል-ካቢ ክለብ በርካን የሴኔጋሉን ምቦር ፔቲትን 2-1 ሲያሸንፍ ግብ ማስቆጠር ችሏል፡፡

የማሊው ጆሊባ እና የቱኒዚያው ዩኤስ ቤን ጎርዳን ተጋጣሚዎቻቸውን ለጨዋታ መድረስ ባለመቻላቸው በቀጥታ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችለዋል፡፡ የላይቤሪያው ኤልዋ ዩናይትድ እና የደቡብ ሱዳኑ አል ሂላል ጁባ ለነበረባቸው ጨዋታዎች ሳይጓዙ ቀርተዋል፡፡

የተመዘገቡት ውጤቶችን እነዚህን ይመስላሉ

ኤኤስ ኦንዜ ክሬቸርስ (ማሊ) 1-1 ሴአር ቤሎዝዳድ (አልጄሪያ)

ንጋዚ ስፖርት (ኮሞሮስ) 1-1 ኤኤስ ፖር ሉዊ 2000 (ሞሪሺየስ)

ኦሎምፒክ ስታር (ቡሩንዲ) 0-0 ኤትዋል ፊላንቴ (ቡርኪና ፋሶ)

ያንግ ቡፋሎስ (ስዋዚላንድ) 0-1 ኬፕ ታውን ሲቲ (ደቡብ አፍሪካ)

ኮስታ ዶ ሶል (ሞዛምቢክ) 1-0 ጅዋኔንግ ጋላክሲ (ቦትስዋና)

ማንጋ ስፖርት (ጋቦን) 0-1 ኤኤስ ማኒማ (ዲ.ሪ. ኮንጎ)

ፔትሮ አትሌቲኮ (አንጎላ) 5-0 ማስተርስ ሴክሪዩቲ (ማላዊ)

ኢኔርጂ ስፖርትስ (ቤኒን) 1-0 ሃፊያ (ጊኒ)

አል ኢትሃድ ትሪፖሊ (ሊቢያ) 1-0 ሳህል (ኒጀር)

ኤኤስ ታንዳ (ኮትዲቯር) 0-0 ላ ማንቻ (ኮንጎ ሪፐብሊክ)

ኒው ስታርስ (ካሜሮን) 2-1 ዴፖርቲቮ ኒፋንግ (ኤኳቶሪያል ጊኒ)

አል መስሪ (ግብፅ) 4-0 ግሪን ቡፋሎስ (ዛምቢያ)

ኤኤፍሲ ሊዮፓርድስ (ኬንያ) 1-1 ፎሳ ጁኒየርስ (ማዳጋስካር)

ኤፒአር (ሩዋንዳ) 4-0 አንስ ሪዩኒየን (ሲሸልስ)

ዚማሞቶ (ዛንዚባር) 1-1 ወላይታ ድቻ (ኢትዮጵያ)

ሲምባ (ታንዛኒያ) 4-0 ገርንዳሜር (ጅቡቲ)

አክዋ ዩናይትድ (ናይጄሪያ) 1-2 ባንጁል ሃውክስ (ጋምቢያ)

አፍሪካ ስፖርትስ (ኮትዲቯር) 1-1 ኤፍሲ ኖዲቦ (ሞሪታንያ)

አሻንቲ ኮቶኮ (ጋና) 1-0 ካራ ብራዛቪል (ኮንጎ ሪፐብሊክ)

አርኤስ በርካን (ሞሮኮ) 2-1 ምቦር ፔቲት (ሴኔጋል)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *