​በአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ ላይ የተጣለው ቅጣት ፀንቷል

የመቐለ ከተማው አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የተላለፈባቸውን የ5 ጨዋታ ቅጣት ይግባኝ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው የአሰልጣኙን ይግባኝ ውድቀ አድርጎታል።

አሰልጣኝ ዮሀንስ በ13ኛው ሳምንት ቡድናቸው ከሲዳማ ቡና ጋር ባደረገው ጨዋታ የሲዳማው ረዳት አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉን በመሳደባቸው የ5 ጨዋታ እገዳ እና 5ሺህ ብር ቅጣት እንደተጣለባቸው የሚታወስ ሲሆን ይግባኝ ጠይቀው ጉዳያቸው እስኪታይ ድረስ ከኤሌክትሪክ እና ኢትዮጵያ ቡና ያደረጉትን ጨዋታ እንዲመሩ ተፈቅዶላቸው ነበር። ሆኖም የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው የአሰልጣኙን ይግባኝ ውድቅ በማድረጉ ቅጣቱ ፀንቶባቸዋል። በተስተካካይ መርሀ-ግብር ከመከላከያ የሚያደርጉትን ጨዋታ እና በሁለተኛው ዙር የመጀመርያ 4 ጨዋታዎች ላይም ቡድናቸውን አይመሩም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *