​አርባምንጭ ከተማ ከሁለት ተጫዋቾች ጋር ተለያየ

የፕሪምየር ሊጉ ክለብ አርባምንጭ ከተማ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ካስፈረማቸው ተጫዋቾች መካከል ከዮናታን ከበደ እና ታዲዮስ ወልዴ ጋር በስምምነት መለያየቱ ታውቋል።

ታዲዮስ ወልዴ ከሊጉ ወርዶ የፈረሰው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ለቆ ወደ አርባምንጭ በማምራት እምብዛም በሜዳ ላይ ያልታየ ሲሆን ዮናታን ከበደም ከሀዋሳ ከተማ ጋር በስምምነት ውሉን አቋርጦ አዞዎቹን በመቀላቀል በጥቂት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወቱ የሚታወስ ነው። አሁን ደግሞ ከክለቡ ጋር ባደረጉት ስምምነት ውላቸውን በማቋረጥ ዛሬ መልቀቂያ መውሰዳቸው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *