​አብዱልከሪም ሀሰን ወደ ሀዋሳ ከተማ አመራ

ባሳለፍነው የውድድር ዘመን በሁለት አመት ውል ኢትዮጵያ ቡናን መቀላቀል ቢችልም ካልተሳካ የአንድ አመት ቆይታ በኃላ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ጅማሮ ላይ ከክለቡ ጋር ተለይይቶ ያለፋትን ጥቂት ወራት ክለብ አልባ ሆና ያሳለፍው አብዱልከሪም ሀሰን ሀዋሳ ከተማን መቀላቀሉ ተረጋግጧል፡፡

የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአጥቂ አማካይ አብዱልከሪም ሀሰን ሀዋሳ ከተማን የተቀላቀለው በአንድ አመት ውል ሲሆን በኳስ ቁጥጥር ላይ አመዝኖ የሚጫወተው የውበቱ አባተ ቡድን ሁለቱ ሁነኛ የፈጠራ ምንጭ የሆኑት ፍሬው ሰለሞን እና ታፈሰ ሰለሞንን በተለያዩ ምክንያቶች በሚያጣበት ወቅት ይፈጠር የነበረውን የአማራጭ እጥረት ይቀርፋል ተብሎ ይገመታል፡፡
በክረምቱ የዝውውር መስኮት በርካታ ተጫዋቾችን ማስፈረም የቻሉት ሀዋሳ ከተማዎች በያዝነው የውድድር ዘመን እምብዛም ስኬታማ ያልነበረ የመጀመሪያ የውድድር አጋማሽ አሳልፈው 18 ነጥብን በመሰብሰብ በ8ተኛ ደረጃ መቀመጥ ችለዋል፡፡ ለሁለተኛው ዙር ያለባቸውን ክፍተቶች ለመቅረፍ በማሰብም ባሳለፍነው ሳምንት ከአዳማ ከተማ ጋር የተለያየውን አጥቂውን አላዛር ፋሲካን ማስፈረማቸው የሚታወስ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *