ሁለት የፊፋ ሰዎች ሰኞ አዲስ አበባ ይገባሉ

ብዙ እያነጋገረ እና እያወዛገበ ለአራት ተከታታይ ጊዚያት ምርጫው እንደሚደረግ ቀን ተቀጥሮለት በተለያዩ ምክንያቶች እየተራዘመ እዚህ የደረሰው የፌዴሬሽኑ የምርጫ ሂደት በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ እና ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ለመገምገም የአለም አቀፉ የእግርኳስ አስተዳዳሪ አካል /ፊፋ/ የላካቸው ሁለት ስማቸውንና በፊፋ ያላቸውን የስራ ድርሻ ማወቅ ያልቻልናቸውን ታዛቢዎች ሰኞ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሏል።

ከፊፋ የሚላኩት ግለሰቦች ለምን ያህል ቀን የማጣራት ስራቸውን እንደሚያከናውኑ ያልታወቀ ቢሆንም ከፌዴሬሽኑ ባገኘነው መረጃ በምርጫው ዙርያ የሚመለከታቸውን አካላት እስካሁን ባለው የምርጫው ሂደት እና አሉ በሚባሉ ጉዳዮች ላይ በመተራስ ያነጋግራሉ፡፡ በሚያደርጉት ማጣራት መነሻነትም ምርጫው መቼ እንደሚደረግ እና ስለሚኖረው አጠቃላይ ነገር ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በሌላ በኩሉ የምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሆነ የአቤቱታ ሰሚ አባላት በሙሉ ነገ (እሁድ) አዲስ አበባ እንዲመጡ እና በጁፒተር ሆቴል እንዲገቡ ከፌዴሬሽኑ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው አውቀናል።

ምርጫው መደረግ ከነበረበት 6 ወር የገፋው የፌዴሬሽኑ ምርጫ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የሚቋጭበትን መንገድ ሰኞ አዲስ አበባ የሚገቡት የፊፋ የታዛቢ ልዑካን ይፈጥራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *