​በረከት ይስሀቅ ዳግም ወደ ድሬዳዋ አምርቷል

ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ከስድስት ወራት ቆይታ በኃላ በሰምምነት የተለያየው የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ በረከት ይስሀቅ ወደ ድሬዳዋ ዳግም ተመልሷል። የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ፣ ደደቢት እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች በ2009 የውድድር አመት በድሬዳዋ ከተማ ከቆየ በኃላ ነበር በክረምቱ ኢትዮጵያ ቡናን የተቀላቀለው። ሆኖም በቡናማዎቹ ቤት ስኬታማ ጊዜ ማሳለፍ ባለመቻሉ በአንድ አመት ኮንትራት ማረፊያውን ወደ ምስራቁ ክለብ አድርጓል።

በተያያዘ ዜናም ድሬዳዋ ከተማ እስከ ውድድር ዘመኑ መጨረሻ በአሰልጣኝ ስምዖን አባይ እየተመራ ሊዘልቅ እንደሚችል እና አዲስ አሰልጣኝ ወደ ክለቡ እንዳማይመጣ ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ ቅርበት ካላቸው ሰዎች አረጋግጣለች፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *