ለወላይታ ድቻ በሀዋሳ ደማቅ አቀባበል ተደረገ

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ዛማሌክን በደርሶ መልስ ጫወታ ከውድድሩ ውጭ ያደረገው ወላይታ ዲቻ ወደ ሀዋሳ ሲደረስ በበርካታ ህዝብ ታጅቦ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

ዛሬ ማለዳ ጠዋት ወደ አዲስ አበባ ሲገባ አቀባበል የተደረገለት ክለቡ 9:00 ገደማ ሀዋሳ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ አንስቶ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ተቀብሎታል። በበርካታ መኪኖች ፣ ሞተር ሳይክሎች እና እግረኞች ታጅቦም ሀዋሳ ከተማ ስታድየም (ሰው ሰራሽ ሜዳ) ወደተዘጋጀው የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም አምርተዋል። የክለቡ የበላይ ጠባቂ እና የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አስራት ጤራ መልዕክት በመልክታቸው “ይህ የእኛ ድል ብቻ አይደለም። የሁሉም ህዝብ ውጤት ነው። ከአሁን በኋላ በሊጉ ያሉ ክለቦች በድቻ ድል ተነሳስተው በቀጣይ ወደ ሌላ ምዕራፍ መግባት አለባቸው። ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ምሸት ላይ የክልሉ መንግስት ለቡድኑ አባላት የእራት ግብዣ በሮሪ ሆቴል ያደረገ ሲሆን ነገ ማለዳ 4 ሰአት ወደ ሶዶ ሲያመራ የተለያዩ ፕሮግራሞች እና ከፍተኛ ሽልማት እንደሚኖር ተነግሯል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *