ወልዋሎ ዮሀንስ ሽኩርን አስፈረመ

ከመልካም አጀማመር በኋላ የውድድር ዘመኑን 12ኛ ደረጃ ይዞ ያጋመሰው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በዝውውር መስኮቱ ተጨዋቾችን ለማስፈረም እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ዮሀንስ ሽኩርን የግሉ በማድረግም በመስኮቱ አራተኛ ዝውውሩን አከናውኗል።
ዮሀንስ ሽኩር አምና በፋሲል ከተማ የመጀመርያ ዙር ውጤታማነት ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የተወጣ ግብ ጠባቂ የነበረ ቢሆንም በሁለተኚው ዙር ከጉዳት ጋር በተያዬዘ እምብዛም ጨዋታ አላደረገም። ይህን ተከትሎም በክረምቱ ከአጼዎቹ ጋር መለያየቱ የሚታወሱ ሲሆን ያለፉትን 6 ወራት ክለብ አልባ ሆኖ ቆይቶ በመጨረሻም ወደ ወልዋሎ በ1 አመት ውል አምርቷል።

የቀድሞ የንግድ ባንክ ግብ ጠባቂ በቅርቡ ከቡድኑ ጋር የተለያየው በለጠ ተስፋዬን ቦታ የሚሸፍን ሲሆን ለመጀመርያ ተመራጭነት ከበረከት አማረ እና ዘውዱ መስፍን ጋር መፎካከር ይጠበቅበታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *