ለወላይታ ድቻ የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል

ዛማሌክን በመለያ ምቶች አሸንፎ ወደ ሁለተኛው ዙር ያለፈውና ትላንት በካይሮ በወጣው የእጣ ማውጣት ስነስርዓት ከታንዛኒያው ያንግ አፍሪካንስ ጋር የተደለደለው ወላይታ ድቻ ትላንት ከሀዋሳ ወደ ሶዶ ሲያመራ በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ አቀባበል ያደረገለት ሲሆን ምሸት ላይ ደግሞ ለቡድኑ አባላት የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡ 

በትላንቱ ዝግጅት ላይ የወላይታ ዞን አስተዳደር በአስተዳዳሪው አቶ አስራት ጤራ አማካኝነት 1 ሚሊየን ብር ለቡድኑ አባላት ሲያበረክት የደቡብ ክልል መንግስት ደግሞ የመቶ ሺ ብር ድጋፍን አድርጓል። በቀጣይ ቀናትም ባለሀብቶች ለክለቡ ተጨማሪ የማረታቻ ሽልማት እንደሚያበረክቱ ተነግሯል፡፡ በሽልማቱ መሰረት ለእያንዳንዱ ተጫዋቾች 25 ሺህ ብር የሚደረሰው ይሆናል።
ወላይታ ድቻ በፕሪምየር ሊጉ 16ኛ ሳምንት መሪው ደደቢትን እሁድ ሶዶ ላይ በ09:00 ያስተናግዳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *