ድሬዳዋ ከተማ ጋናዊ ተጫዋች አስፈረመ

በፕሪምየር ሊጉ ወራጅ ቀጠና ላይ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ ጋናዊው ሁለገብ ሚካኤል አኩፎን አስፈርሟል፡፡

የቀድሞው የአሻንቲ ኮቶኮ ተጫዋች በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ለመቐለ ከተማ ፊርማውን አኑሮ የነበረ ቢሆንም በመጀመርያው የውድድር ዘመን አጋማሽ ክለቡ ባሰበው መልኩ አጥጋቢ አቋም ባለማሳየቱ ከተቀነሱ 7 ተጫዋቾች መካከል አንዱ ሆኖ ከቡድኑ ጋር ተለያይቷል፡፡ ወደ ምስራቁ ክለብ አምርቶም በአንድ አመት ኮንትራት በመስማማት ድሬዳዋ ከተማን ተቀላቅሏል፡፡

በተከላካይ እና አማካይ መስመር ላይ መጫወት የሚችለው ሚካኤል አኩፎ በቅርቡ ክለቡን ለቆ ወደ ፋሲል ከተማ ያመራው ሌላው ሁለገብ ተጫዋች ሰንደይ ሙቱኩን ክፍተት ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዝውውር መስኮቱ ሁለት ተጫዋቾች የለቀቀው ድሬዳዋ ከተማ እስካሁን ዮሴፍ ድንገቱ ፣ ሚካኤል አኩፎ እና በረከት ይስሃቅን ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *