ፌዴሬሽኑ የሪቻርድ አፒያን የቅዱስ ጊዮርጊስ ዝውውር ውድቅ አደረገ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በያዝነው የዝውውር መስኮት አስፈርሞት የነበረው ጋናዊው አጥቂ ሪቻርድ አፒያ ዝውውሩ በፌዴሬሽኑ ውድቅ መደረጉ ታውቋል፡፡

የቀድሞው የኸርትስ ኦፍ አክ እና አሻንቲ ኮቶኮ አጥቂ በውድድር አመቱ ክለብ አልባ ሆኖ የቆየ ሲሆን እስከ ውድድር ዘመኑ መጨረሻ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ለመጫወት ከስምምነት ላይ ደርሶ ነበር፡፡ ሆኖም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከፊፋ ጋር ባደረገው ግንኙነት መሰረት ዝውውሩን ውድቅ ማድረጉን ለክለቡ በደብዳቤ ገልጿል፡፡

አማራ ማሌ እና ሳላዲን ሰዒድን በጉዳት ያጣው እና ኬይታ ሴዲን የሸኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ዝውውሩ ውድቅ የሚሆንበት ምንም አይነት የህግ አግባብ የለውም በሚል በጉዳዩ ላይ እንደሚገፋበትም ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *