ዋሊያዎቹ የአንጎላ አቻቸውን በሚመጣው እሁድ ሉዋንዳ ላይ ይገጥማል፡፡ ዋሊያዎቹ በሀዋሳ ሲደርጉት የነበረውን ጠንካራ ልምምድ አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ የተመለሱ ሲሆን ረቡእ እለት ወደ ሉዋንዳ የሚያቀኑ ይሆናል፡፡ ብሄራዊ ቡድኑ ከአንጎላ አቻው ጋር ከተጫወተ በኅላ ወደ ብራዚል በማቅናት ከ5 ክለቦች ጋር ጨዋታ እንደሚያደርግ የፌድሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ጁነይዲ ባሻ በትዊተር ገፃቸው ገልፀዋል፡፡ አቶ ጁነዲ በተጨማሪም ከግብፅ እና ቤኒን ብሄራዊ ብድኖች የቀረበላቸውን የወዳጅነት ጨዋታ ከግዜ መጣበብ ጋር ያልተቀበሉት ሲሆን ከግብፅ ጋር የመጫወት እድሉ አሁንም አንዳለ ግን ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአልጄሪያ ጋር ላለበት ወሳኝ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ከአንጎላ ጋር እና ከተለያዩ የብራዚል ክለቦች ጋር ለመጫወት መወሰኑ ከአንዳንድ የስፓርት ቤተሰብ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ አሁንም ከአልጄሪጋር ተቀራራቢ የጨዋታ ስልት ካላት ግብፅ ጋር መጫወቱን ምርጫ እንደሚያደርጉ አንዳንድ የዋሊያዎቹ ደጋፊዎቹ ጠቅሰዋል፡፡